በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምርጫ ውጤቱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ መንግስት ማስጠንቀቂያ ሰጠች


“ኢትዮጵያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ላላት ግንኙነት ክብደት የምትሰጥ ከሆነ ለዚህ በጣም ቀጥተኛና ጠንካራ መልዕክት ጽኑ ትኩረት መስጠት አለባት”

የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፒ.ጄ ክራውሊ የኢትዮጵያውያን የመምረጥ መብት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግስት፥ ብሄራዊው የምርጫ ቦርድ፥ ገዢው ፓርቲና ደጋፊዎቹ በመላው የምርጫ ሂደት በፈጸሙዋቸው ተግባሮች ተገድቧል ብለዋል።

የኦባማ አስተዳደር በጸጥታና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያን ትብብር ቢፈልገውም በምርጫው አካሄድ ላይ ቅሬታ እንዳለው ገልጾ፤ ግንኙነታቸው የኢትዮጽያ መንግስት ምርጫውን አስመልክቶ ለተንጸባረቁ ስጋቶች ምላሽ በመስጠቱና ባለመስጠቱ ላይ ሊወሰን እንደሚችል በመጥቀስ አስጠንቅቋል።

የኦባማ አስተዳደር ይህን ያለው፣ ጊዜያዊው የምርጫ ውጤት ገዢው ፓርቲና ተባባሪዎቹ ከ500 በላይ በሆኑት የምክር ቤቱ መቀመጫዎች ከሶስት በስተቀር በሙሉ መያዙን ካመለከተ በኋላ ነው።

በሀገሪቱ ከአምስት አመታት በፊት ከተካሄደው ምርጫ በኋላ የወጡት የምርጫ ህጎችና ስነምግባሮች ግልጽና ወሳኝ በሆነ መንገድ የገዢውን ፓርቲ ጥምረት የሚጠቅሙ ናቸው ሲሉ ቃል አቀባይ ፒ.ጄ ክራውሊ አስገንዝበዋል።

ፒ.ጄ ክራውሊ
ፒ.ጄ ክራውሊ

“ኢትዮጵያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ላላት ግንኙነት ክብደት የምትሰጥ ከሆነ ለዚህ በጣም ቀጥተኛ፤ ጠንካራ መልዕክትና ጽኑ ትኩረት መስጠት አለባት። እኛ ክልላዊ ጸጥታንና የአየር ለውጥን በመሳሰሉና በሌሎች ጉዳዮች ከኢትዮጽያ ጋር ላለን ግንኙነት ክብደት ሰጥተን እንመለከተዋለን። ስለሆነም ከዚህ መንግስት ጋር አብሮ መስራቱን እንቀጥላለን። ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት ዲሞክራስያዊ ተቋማትን ለማሻሻል መውሰድ ያለበት እርምጃዎች እንዳሉ ግልጽ እናደርጋለን” ሲሉ ቃል አቀባይ ፒ.ጄ ክራውሊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጽያ መንግስት በበኩሉ ምርጫው ነጻ፥ ፍትሃዊና ዲሞክራስያዊ ነበር ብሏል።

XS
SM
MD
LG