በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሲያም አሊ አብዱ


ከሥድስት ዓመታት በፊት ኤርትራ ከሱዳን ጋር የምትዋሰንበትን ድንበር ለማቋረጥ ከሞከረች በኋላ የተሰወረችው የሲያም አሊ አብዱ ቤተሰብ የት እንዳለች እየጠየቀ ነው።

ከሥድስት ዓመታት በፊት ኤርትራ ከሱዳን ጋር የምትዋሰንበትን ድንበር ለማቋረጥ ከሞከረች በኋላ የተሰወረችው የሲያም አሊ አብዱ ቤተሰብ የት እንዳለች እየጠየቀ ነው።

ሲያም የተወለደችው ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ሲሆን ገና በወጣትነት እድሜዋ ነበር ወደ አስመራ የተዛወረችው።

ወላጅ አባቷ አሊ አብዱ አህመድ በመንግሥቱ ውስጥ የፕሬዘዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ምሥጢረኛና ከፍተኛ ባለሥልጣን ነበሩ።

እአአ በ2012 ዓ.ም ያኔ ሲያም የ15 ዓመት ወጣት ሳለች አባቷ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር ነበሩ። ድንገትና እስካሁን ምክንያቱ ባልተገለፀ ሁኔታ አሊ አብዱ ከፕሬዘዳንቱ አስተዳደር ራሣቸውን በማግለል ከኤርትራ ወጡና ወደ አውስትራሊያ ተሰደው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቁ - ከቤተሰቦቻቸው ተለያዩ።

ያ ከሆነ ከሣምንታት በኋላ ነበር ኪያም ወደ ሱዳን ለመኮብለል ስትሞክር የተያዘችው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቧ ስለርሷ ሰምቶም፣ አይቷትም አያውቅም።

የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ቡድኖችና ቤተሰቧ እምነት ኪያም እስካሁን በእሥር ቤት እየተሰቃየች እንደምትኖር ነው።

የኤርትራ መንግሥት ሲያም አሜሪካዊ ዜግነት ያላት ስለመሆኑም ይሁን በሕይወት ስለመኖሯ ማመን አይፈልግም።

ቤተሰቦቿ ልጃቸው ልትፈታ የምትችለው በውጭ ተፅዕኖ እንደሚሆን ተስፋ ያደርጋሉ። በተለይ የአሜሪካ ዜጋ በመሆኗ ዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ሚና ልትጫወት ትችላለች ይላሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG