በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰበር ዜና - የአሜሪካ ኤምባሲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተቃወመ


የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፤ አዲስ አበባ
የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፤ አዲስ አበባ

መሰብሰብና ሃሣብን መግለፅን መከልከልን ጨምሮ በመሠረታዊ መብቶች ላይ ክልከላ የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ የኢትዮጵያ መንግሥት በወሰደው ውሣኔ በብርቱ እንደማይስማማ አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታወቀ። “ሁከትና የሰው ሕይወት የጠፋባቸውን አጋጣሚዎች የምንረዳና የኢትዮጵያ መንግሥትም ያሉትን ሥጋቶች የምንጋራ ብንሆንም መልሱ ግን ነፃነትን ማሳነስ ሳይሆን ማብዛት እንደሆነ በብርቱ እናምናለን” ብሏል የኤምባሲው መግለጫ።

መሰብሰብና ሃሣብን መግለፅን መከልከልን ጨምሮ በመሠረታዊ መብቶች ላይ ክልከላ የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ የኢትዮጵያ መንግሥት በወሰደው ውሣኔ በብርቱ እንደማይስማማ አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታወቀ።

“የሁከትና የሰው ሕይወት የጠፋባቸውን አጋጣሚዎች የምንረዳና የኢትዮጵያ መንግሥትም ያሉትን ሥጋቶች የምንጋራ ብንሆንም መልሱ ግን ነፃነትን ማሳነስ ሳይሆን ማብዛት እንደሆነ በብርቱ እናምናለን” ብሏል የኤምባሲው መግለጫ።

ኤምባሲው አክሎም “ዴሞክራሲያዊ ማሻሻያዎችን በማድረግ በኩልም ይሁን የምጣኔ ኃብት እድገትን በማስመዝገብ፣ ወይም ዘላቂ መረጋጋትን በማስገኘት መስክ ኢትዮጵያ ያሉባትን ፈተናዎች በተሻለ ሁኔታ ልትወጣቸው የምትችለው ክልከላዎችን በመደንገግ ሳይሆን አሳታፊ በሆኑ ንግግሮችና በፖለቲካ ሂደቶች ነው” ብሏል።

“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣቱ በሺሆች የሚቆጠሩ እሥረኞችን መልቀቅን ጨምሮ ይበልጥ አካታች የሆነ የፖለቲካ መስክ ለመፍጠር በቅርቡ የተወሰዱ አዎንታዊ እርምጃዎችን የሚያደናቅፍ ነው” ያለው የአዲስ አበባው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ “ኢትዮጵያዊያን ሃሣቦቻቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለፅ እንዳይችሉ የሚያደርግ ገደብ መጣሉ የሚያስተላልፈው መልዕክት የሕዝቡ ድምፅ አለመሰማቱን ነው” ብሏል።

“ለዘላቂ ዴሞክራሲ መንገድ ለመክፈት እንዲቻል ትርጉም ላለው ንግግር፣ እንዲሁም የፖለቲካ ተሣትፎ መስኩን በተግባር በማስፋትና በመጠበቅ መንግሥቱ ይህንን አካሄዱን በድጋሚ እንዲያጤነውና ሕይወቶችንና ንብረትን ከአደጋ ሊጠብቅ የሚችልባቸውን ሌሎች መላዎችን እንዲሻ አጥብቀን እናሳስባለን” ሲል የአሜሪካ ኤምባሲ መልዕክቱን ደምድሟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG