አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ነገ፣ መስከረም 9/2019 ዓ.ም. ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል።
ኤምባሲው ለነገ አገልግሎቱን የሚያቋርጠው በከተማዪቱ ውስጥ በሚካሄደው “ግዙፍ ሊሆን ይችላል” ባለው ሰልፍ ምክንያት የተጠናከረ ጥንቃቄ ለመውሰድ ሲባል መሆኑን ገልጿል።
ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩ የቪዛ ቀጠሮዎችና ኤምባሲው ለአሜሪካዊያን ዜጎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ለነገ መስከረም 9/2019 ዓ.ም /19 September 2018/ ተቀጥረው የነበሩ ጉዳዮች በሙሉ የተሠረዙ መሆናቸውን አስታውቋል።
አሜሪካዊያን በኤምባሲው ዌብሳይት አማካይነት አዲስ ቀጠሮ እንዲይዙ መክሯል።
ከኢሚግራንት ቪዛ ጠያቂዎች ጋር ተለዋጭ ቀጠሮ ለማድረግ ኤምባሲው በቅርቡ የሚያገኛቸው መሆኑንና ነን-ኢሚግራንት ቪዛ ለማግኘት ያመለከቱ ደግሞ በኤምባሲው ዌብሳይት ላይ አዲስ ቀጠሮ እንዲጠይቁ አሳስቧል።
አጣዳፊ አገልግሎት የሚፈልጉ አሜሪካዊያን ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዌብሳይት ላይ ያለውን የአድራሻ/የመገናኛ መረጃ እንዲያዩ መክሯል።
ከኤምባሲው መደበኛ አገልግሎቶች በተጨማሪ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካ ማዕከል እና ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ውስጥ የሚገኘው ሳችሞ ማዕከልም ነገ ዝግ ሆነው እንደሚውሉ አስታውቋል።
በሰልፉ ላይ የሚሣተፉ ሁሉ ሃሣቦቻቸውንና ፍላጎቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለፃቸውን እንደሚያበረታታም ኤምባሲው ገልጿል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ