ዩናይትድ ስቴትስ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ በኦነግ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር በቴ ዑርጌሳ ግድያ ላይ እያደረገ ያለው ምርመራ እክሎች ሊፈጠሩበት እንደማይገባ አሳሰበች።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲም፣ አሁንም የአቶ በቴ ግድያ እንዲጣራ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካውንስል በበኩሉ፣ የአቶ በቴ ግድያ መጣራቱ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለሚሳተፉ ወገኖች ወሳኝ እንደኾነ ሲገልጽ፤ ኦነግ ደግሞ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ አሁን በእጁ የሚገኘውን የግድያ ምርመራ ውጤት ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል። ኮሚሽኑ፣ በመቂ ከተማ ሲያከናውን የቆየው የአቶ በቴ ዑርጌሳ ግድያ ምርመራ መቋረጡን ገልጿል። በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት አካል ምላሽ ማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡
መድረክ / ፎረም