ኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ላይ ያነጣጠረ የሮኬት ጥቃት ዛሬ ዓርብ ጠዋት መድረሱ ተገለጠ፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራቅ ባለስልጣናት እንዳሉት በጥቃቱ በንብረት ላይ አነስተኛ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፡፡
የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ “ግሪን ዞን” በሚባለው ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት የባግዳድ አካባቢ በሚገኘው ኤምባሲ ላይ በኢራቅ ባለስልጣናት የተረጋገጠ ጥቃት ሲደርስ የዛሬው የመጀመሪያ መሆኑ ነው፡፡
ከሁለት ወራት በፊት እስራኤል በሐማስ ላይ ጦርነት ካወጀች ወዲህ ኢራቅ ያሉ በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎች ኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ሰፈሮች ላይ ለተሰነዘሩ በርካታ ጥቃቶች ኅላፊነት ወስደዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት የዩናይትድ ስቴትስ አካላት ባሉባቸው ሥፍራዎች ላይ 78 ጥቃቶች መሰንዘራቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኅይል አስታውቋል፡፡ 37ቱ ኢራቅ አና 41ዱ ሶሪያ ውስጥ የሚገኙ ስፍራዎች መሆናቸውን አመልክቷል፡፡ ዛሬ የተተኮሱት 14 ካትዩሻ ሮኬቶች ሲሆኑ የተወሰኑት የኤምባሲው ግቢ በር አጠገብ ሌሎቹ ደግሞ ወንዙ ውስጥ መውደቃቸውን አንድ የኢራቅ የጸጥታ ባለስልጣን ተናግረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም