ናይሮቢ —
አልቃይዳ በናይሮቢና ዳሬሰላም በሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲዎች ላይ ያደረሰዉ ጥቃት ዛሬ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ታስቦ ውሏል።
ጥቃቱ የተፈፀመው የዛሬ 20 ዓመት ነሐሴ 7/1998 ሲሆን በጊዜዉ ከ250 በላይ ሰዎች ሕይወታቸዉ ማለፉ የሚታወስ ነው። ዛሬ በተደረገው የመታሰብያ ሥነ ሥርዓት ላይ በኬንያ የአሜርካ አምባሳደር ሮበርት ፍራንክ ጎዴክ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።