ዋሺንግተን ዲሲ —
በዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ጊዜ ታሪክ የዘንድሮውን ዓይነት ከፋፋይ ምርጫ ታይቶ አይታወቅም ተብሏል።
በሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች መሠረት ሂላሪ በሁለቱም በምርጫ ውጤት ላይ ወሳኝነት አላቸው በሚባሉ ክፍለ ግዛቶች፥ ባነስተኛ የድምፅ ብልጫ ያለማቋረጥ ተቀናቃኛቸውን ዶናልድ ትራምፕን እየመሩ ናቸው።
ባልደረባችን ጂም ማሎኒ ሁለቱ ዕጩ ተወዳዳሪዎችና ደጋፊዎች ለማግኘት በመጨረሻዋ ደቂቃ እያካሄዱ በአሉት እልህ አስጨራሽ ትግል ዙሪያ ተከታዩን ዘግቧል ሰሎሞን ክፍሌ ያቀርበዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡