በአሜሪካ ምርጫ በሃገሪቱም ኾነ በተቀረው ዓለም ላይ አንድምታ የሚኖራቸው ጉዳዮች ይነሳሉ። የኢኮኖሚ፣ የፍልሰተኖች፣ የውጪ ጉዳይና የመከላከያ ጉዳዮች ከሚጠቀሱት ውስጥ ፖሊስዎች ውስጥ ናቸው። በተጠቀሱትም ሆነ በሌሎቹ ጉዳዮች ላይ ሁለቱ እጩዎች፣ ዶናልድ ትረምፕ እና ካመላ ሄሪስ የሚለያዩት በምንድን ነው? ጉዳዮቹስ በተቀረው ዓለምም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ላይ የሚኖራቸው ተጽእኖ ምን ይሆን?
ባልደረባችን እንግዱ ወልዴ በጆርጂያ ስቴት ዩኒቨርስቲ፣ ፐሪሜትር ኮሌጅ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑትን ዶ/ር ፋሲል ቸርነት አነጋግሯል።
መድረክ / ፎረም