በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምርጫው ደህንነት የተጠበቀ ነው


እጩ ፕሬዚዳንቶቹን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ ተወካዮችን ለመምረጥ በመላው አሜሪካ በመካሄድ ላይ ያለው የምርጫ ሂደት፣ ደህንነቱ በአስተማማኝ የተጠበቀ መሆኑን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እየተከታተሉ ነው፡፡ የምርጫው ሂደት ቀጣይ ሊሆን ስለሚችልም በንቃት መጠባበቅም ተገቢ ነው እየተባለ ነው፡፡ የብሄራዊ ደህንነት ዘጋቢያችን ጄፍ ሴልዲን እንደዘገበው እጩ ፕሬዚዳንቶቹን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ ተወካዮችን ለመምረጥ በመላው አሜሪካ የሚካሄደው የምርጫ ሂደት፣ ደህንነቱ በአስተማማኝ የተጠበቀ መሆኑን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እየተከታተሉ ነው፡፡

ቀደምሲል በተለያየ መንገድ ድምጻቸውን አስቀድመው ከሰጡት 100 ሚሊዮን መራጮች በተጨማሪ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች አሜሪካውያን የመጨረሻ በሆነው በዛሬው እለት፣ በአካል ተገኘተው ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንም እንኳ በአሜሪካ ባላንጣዎች የምርጫው ሂደት ሊሰናከልና ሊታወክ ይችላል የሚል ስጋትና ግምት ቢኖርም ገና ከማለዳው የታየው ስጋቱ ያሳደረው ተጽእኖ አነስተኛ መሆኑና የተሞከረም ነገር ካለ፣ የከሸፈ መሆኑን ነው ባለሥልጣናቱ የሚናገሩት፡፡

የአገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትሩ ቻድ ዎልፍ ድምጽ መስጫዎቹ በይፋ ተከርተው ምርጫ ከተጀመረ ሰዐታት በኋላ ሲናገሩ

“የውጭ ባላንጣዎቻችን ይህኛውን የምርጫ ሂደትና ድምጽ አሰጣጥ በመፈታተን ረገድ የተሳካላቸው ሙከራ ስለመኖሩ ምንም ምልክት አላየንም”የምርጫ ሥርዐትና መዋቅራችና አስተማማኝ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ንቁ ሆነነ መጠበቅ ይኖርብናል” ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ባለሥልጣናት በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የምርጫውን ሂደት ጥሶ በመግባት ለማደናቀፍ ቢያንስ ሁለት ሙከራዎች መኖራቸውን አምነዋል፡፡ አንደኛ ከኢራን ሲሆን ሌላኛው ከራሽያ ነው፡፡ ሁለቱም አገሮች ሊያደርጉ የሞከሩት የመራጮችን ምዝበገባና የግል የመረጃ ቋትን መመዝበር ነው ፡፡ በተለይ የኢራን ኢንተርኔት መዝባሪዎች፣ የአንድን ክፍለ ግዛት መረጃ ቋት በመስረቅ፣ ለመራጮች የተሳሳተ ቅስቀሳ እንዲሰራጭ የማድረግ ሙከራ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡ ያም ሆኖ ግን ሁኔታው ቶሎ ተደርሶበት ወዲያውኑ የተዘጋ በመሆኑ በዛሬው ምርጫ ሂደትም ሆነ በምርጫው ውጤት ላይ ምንም የሚያስክትለው ነገር አይኖርም ተብሏል፡፡

“የተወሰደ ምንም ዓይነት የመራጮ መረጃ የለም” የሚሉት ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በአሜሪካ የሳይበር ጥቃትና የኢንተርኔት ደህንነት ኤጀንሲ ከፍተኛ ባለሥልጣን ናቸው፡፡ ከሪፖርተሮች ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ እንዲህ ብለዋል፡፡

“የመራጮች ድምጽ የተጠበቀ መሆኑን፣ ድምጹም የሚቆጠርና፣ ውጤቱም ተረጋግጦ የሚገለጽበት ሂደት የተጠበቀ መሆኑን እርግጠኛ ነን፡፡ እርግጠኛም እንደሆን እንቆያለን፡፡”

አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ረጅም ሰልፎች ኖሯቸው የታዩት ገና እንደተከፈቱ ነበር፡፡ “ኤሌክሽን ኦርግ” የተባለውና ራሱን ገለልተኛ አድርጎ የሚገልጸው ተቋም እንደሚለው፣ ብዙ ሰልፍ የሚታየው በመራጮች ብዛት የተነሳ ነው፡፡

ይህም ሆኖ ግን የአሜሪካ ባለሥልጣናት፣ አሁንም ቢሆን ሰዎች ሁኔታዎችን በንቃት እንዲከታተሉ መክረዋል፡፡ እንደ ራሺያ፣ ቻይና እና ኢራን የመሳሰሉ አገሮች፣ ምርጫው እስኪጠናቀቅ ድረስ ብዙ ጥቃቶች ሊያደርሱ ይችላሉ ብለዋል፡፡ የኢንተርኔት ደህንነት ኤጀንሲ ድሬክተር፣ ክሪስቶፈር ከርብስ እንዲህ ይላሉ

“አሁንም ገና ከስጋቱ አልወጣንም፡፡ ዛሬ ገና አጋማሹ ላይ እንሆናለን፡፡ በምርጫው ሂደት ሌሎች ተከታይ ክስተተቶች ወይም እንቅስቃሴዎች ስለሚኖሩን፣ እነሱን ሊያውኩና በምርጫው ሂደት እንዳተማመን፣ የበለጠ ውዥንብር ሊፈጥሩ የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ስለዚህ ሁሉንም የማሳስበው አሜሪካውያን በትዕግስት እንዲጠባበቁና ሁሉንም ቅስቀሳና እወጃ በጥርጣሬ እንዲመለከቱ ነው፡፡”

የጸረ ስለላና ደህንነት ተቋማት ባለሥልጣናት እንደሚያስጠነቅቁት እንደ ሩሲያ፣ ቻይናና በተለይም ኢራን፣ አሜሪካውያንን ለይተው ለማጥቃት፣ አሁን የተፈጠረውን የፖለቲካ መከፋፈልና በዚህ ምርጫ ሂደት የተፈጠረውን አለመተማመን መጠቀም ይፈልጋሉ፡፡ የሶስቱንም አገሮች በኃላፊነት የሚከታተሉ ባለሥልጣናትም እንደሚሉት፣ የተባሉት ሶስቱ አገራት፣ በአንድ ሆነ በሌላ መንገድ ወይ ፕሬዚዳንት ትራምፕን ወይም የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን መጉዳት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የምርጫው ደህንነት የተጠበቀ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:35 0:00


XS
SM
MD
LG