በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደን የድል ንግግር፤ ስለምርጫው ውጤት የዓለም ምላሽ


ተመራጮቹ ፕሬዚዳንት ባይደንና ም/ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ ከነቤተሰቦቻቸው /ዌልሚንግተን፤ ዴላዌር - ቅዳሜ፤ ጥቅምት 28/2020/
ተመራጮቹ ፕሬዚዳንት ባይደንና ም/ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ ከነቤተሰቦቻቸው /ዌልሚንግተን፤ ዴላዌር - ቅዳሜ፤ ጥቅምት 28/2020/

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለአንድነትና ተከፋፍሎ የተራራቀውን የፖለቲካ አካሄድ ለማቀራረብ የሚጣራ ንግግር አድርገዋል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት የድል ንግግራቸውን ያደረጉት የዘንድሮው ምርጫ ውጤት ወደ እርሣቸው ማጋደሉ ከተነገረ ከሰዓታት በኋላ ነበር።

ምክትላቸው ካማላ ሃሪስም በተስፋና በማነቃቃት ቃላት የተሞላ ንግግር አሰምተዋል።

በዘንድሮው የምርጫ ውጤት ትውልዳቸው አፍሪካ የሆነ አሜሪካዊያንም ከፍ ላሉ የህዝብ ውክልና ቦታዎች ተመርጠዋል፤ የኢትዮጵያ ልጆችም አሉበት።

ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ውጤቱን እስካሁን ባይቀበሉትም ለተመራጩ ፕሬዚዳንትና ለምክትላቸው የደስታ መልዕክቶች ከውጭ እየደረሷቸው ነው።

የባይደን-ሃሪስ ደጋፊዎች የሃገሪቱን ትላልቅ ከተሞች ጎዳናዎች አጥለቅልቀው ውለዋል፤ አምሽተዋል። የትረምፕ ደጋፊዎች ደግሞ ተቃውሟቸውንና ቅሬታዎቻቸውን የገለፁባቸቅን ሰልፎች አድርገዋል፤ በተለያዩ መድረኮችና አጋጣሚዎችም እየገለፁ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የባይደን የድል ንግግር፤ ስለምርጫው ውጤት የዓለም ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:24 0:00


XS
SM
MD
LG