በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ባንክ ከመጋቢት ጀምሮ ወለድ ሊጨምር ይችላል ተባለ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ባንክ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ባንክ

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ባንክ ከመጋቢት ወር ጀምሮ የወለድ መጠኑን ለማሳዳግ እና በኮቪድ-19 ለተጎዳው የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት የሚያደርገውን የፋይናንስ ድጋፍ የሚያቋርጥ መሆኑን ማመላከቱ ተገለጸ፡፡

ማዕከላዊ ባንኩ የኮሮናቫይረስ ወረሽኝ ዩናይትድ ስቴትስ ማጥቃት ከጀመረበት እኤአ መጋቢት 2020 ጀምሮ ወደ ዜሮ አውርዶት የነበረው የወለድ መጠን ምጣኔ ሀብቱን ከተጠበቀው በላይ እንዲያገግምና የሥራ አጥነቱን ቁጥር የቀነሰ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ከዐመት ዓመት 7 ከመቶ የጨመረው የሸማቾች ዋጋ በታህሳስር ወር በአስርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡ ተነግሯል፡፡

የፌደራል ባንኩፖሊሲ አውጭዎች በዋሽንግተን ለሁለት ቀናት ሰብሰብ ስለጭማሪው የወሰኑ ቢሆንም ወለዱ የሚጨምርበትም መጠን አልገለጹም፡፡

ይሁን እንጂ ባንድ ጊዜ ከፍተኛ ጭማሪ የማይጠበቅ ቢሆን እንኳ በጊዜ ሂደት ውስጥ ሰዎች ለሚጓዟቸው ቤቶችና ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የብድር ወለድ እንዲሁም አምራቾች በትላልቅ የማምረቻ መሳሪያዎቻቸው ግዢና ሸቀጦቻቸው ላይ ከፍተኛ ክፍያ ሊከፍሉ እንደሚችሉ የሚጠበቅ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG