በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሩሲያ ተዋጊ ጀት ጋር የተጋጨው የዩናይትድ ስቴትስ ድሮን


This handout photo, courtesy of the U.S. Air Force, obtained on Nov. 7, 2020, shows an MQ-9 Reaper drone.
This handout photo, courtesy of the U.S. Air Force, obtained on Nov. 7, 2020, shows an MQ-9 Reaper drone.

ከዩናይትድ ስቴትስ ትልቅ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጋር በጥቁር ባህር ሰማይ ላይ የተጋጨው የሩሲያ ተዋጊ ጀት ብዙም ያልተመለደና አደገኛ መሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶችን ቁጣ መቀስቀሱ ተነገረ፡፡

ሩሲያ ሚስጥራዊ ቴክኖሎጂ ልታገኝ ትችላለች የሚል ስጋት መፍጠሩም ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ ባለሥልጣናት እንዲህ ባለው የMQ-9 ሬፐር ድሮን እና በሩሲያ ኤስዩ 27 ተዋጊ ጀት መካከል ስለተፈጠረው ግጭት እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የሩሲያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ ግን “ሩሲያ ግጭት እየፈለገች አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አምባስደሩ አክለውም “በዩናይትድ ስቴትስና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል ምንም ዓይነት ግጭት አንፈልግም፡፡ እኛ ለዩናይትድ ስቴትስና ሩሲያ ፌዴሬሽን ህዝቦች ስንል ትርጉም ያለው ግንኙነት እንዲኖር እንፈልጋለን፡፡” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን ቃል አቀባይ ብርጌደር ጀኔራል ፓት ሬደር “እኛ የተመለከትነው ነገር ተዋጊ አውሮፕላኖች ከዚህ ድሮን ፊት ለፊት ነዳጅ ሲደፉና ወደ MQ-9 ድሮን ሰው አልባ አውሮፕላን ተሽከርካሪ አካል ተጠግተው ጉዳት ማድረሳቸውን ነው፡፡ በሩሲያ ተዋጊ አውሮፕላንም ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንደማይቀር እንገምታለን፡፡ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጄኔራሉ አክለውም “እኛ እስከምናውቀው ድረስ ተዋጊ አውሮፕላኑ፣ የሩሲያ ተዋጊ አውሮላን አርፏል፡፡ የት ነው ያረፉት ወደ ሚለው መሄድ አልፈልግም፡፡ ግን አሁንም የምለው በእነዚህ ፓይለቶች ዘንድ እጅግ ሙያዊ ያልሆነ ደህንነቱ ያልተጠበቀ የአብራሪነት ሥራ መኖሩን አሳይቷል፡፡” ብለዋል፡፡

የደረሰው ክስተት በሞስኮው የዩክሬን ጦርነት ላይ ውጥረት ፈጥሯል፡፡ ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ሰው አልባ አውሮፕላን በሩሲያ የጦር አውሮፕላን ተመቶ ሲወድቅ ይህ የመጀመሪያው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG