ፓናማ በትራምፕ አስተዳደር የሚባረሩ ዜጎችን ለማሳረፍ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት፤ ከሌሎች ሀገራት የተላኩ ስደተኞችን የጫነውን የመጀመሪያውን የአሜሪካ በረራ ተቀብላለች።
ፕሬዝዳንት ሆዜ ራውል ሙሊኖ በሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ “ትላንት የዩናይትድ ስቴትስ አየር ሃይል 119 ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተውጣጡ ሰዎችን ይዞ መጥቷል” ያሉ ሲሆን፤ አያይዘውም ከቻይና፣ ኡዝቤኪስታን፣ ፓኪስታን፣ አፍጋኒስታን እና ከሌሎችም ሀገራት የመጡ ስደተኞች መኖራቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ የአሁን በረራ በድምሩ ወደ 360 ሰዎችን ለማምጣት ከታቀዱ ሦስት በረራዎች መካከል የመጀመሪያው ነው ብለዋል። “እምብዛም ትልቅ ነገር አይደለም” በማለት አክለዋል።
ስደተኞቹ ወደ አገራቸው ከመመለሳቸው በፊት በፓናማ ዳሪየን ግዛት ወደሚገኝ መጠለያ ይወሰዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ሙሊኖ ተናግረዋል።
ፓናማ ለሚባረሩ ስደተኞች ለምን እንደ ማቆያ ለመሆን እንደፈቀደች ባለፈው ሐሙስ የተጠየቁት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካርሎስ ሩይዝ ሄርናንዴዝ የአሜሪካ መንግስት በመጠየቁ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የአሜሪካ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢሚግሬሽን ኤጀንሲዎች በኩል ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያስፈልገውን ገንዘብ እየከፈለ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚስትሩ አክለውም ረቡዕ እለት ወደ ፓናማ የገቡት ስደተኞች የዩናይትድ ስቴትስ ድንበር በህገወጥ መንገድ ያቋረጡ እንጂ ወንጀለኞች አይደሉም ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ባለፈው ሳምንት በፓናማ ከሙሊኖ ጋር ተገናኝተው ነበር። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓናማ ቦይን እንደገና ለመቆጣጠር ያቀረቡት ጥያቄ በጉብኝቱ ላይ አብላጫ ትኩረት ነበረ። ፕሬዝዳንት ሙሊኖ በፓናማ በኩል በዳሪን ክፍተት ፍልሰትን ለማዘግየት በሚደረገው ጥረት ላይ ፓናማ የአሜሪካ ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንድትልክ እንደ ድልድይ እንድታገለግል ጥያቄ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ወደ ጓቲማላ እና ኤል ሳልቫዶር ባደረጓቸው ጉዞዎች፤ ሀገራቱ ከሌላ ሀገር የመጡ ስደተኞችን ለመቀበል ስምምነትን አግኝተዋል።
ፓናማ እና ኮሎምቢያን የሚያገናኘው በዳሪን ክፍተት በኩል የሚደረግ ፍልሰት ባለፈው ባለፈው ዓመት በጥር ወር ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በ90 ከመቶ ቀንሷል።
ሙሊኖ ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት ወደ ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ፤ ፓናማ በደርዘን የሚቆጠሩ ስደተኞችን የማባረር በረራዎችን አድጋለች። አብዛኛዎቹ በረራዎች በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት የተደረጉ ናቸው።
ሩይዝ ሐሙስ ዕለት ፓናማ “በቀረበላት ጥያቄ መሰረት ለመሳተፍ እና ለመተባበር ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ ነች" ብለዋል።
መድረክ / ፎረም