በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ የሰጡት መግለጫ


ጆን ከርቢ /የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ/
ጆን ከርቢ /የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ/

የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በተካሄዱ ተቃውሞዎችና አመፆች የተነሳ ባለፈው ቅዳሜ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተገንዝበናል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በተካሄዱ ተቃውሞዎችና አመፆች የተነሳ ባለፈው ቅዳሜ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተገንዝበናል።

አዋጁ ሊያስከትል የሚችለው ተፅዕኖም አለ።

ለምሳሌ የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋት ጨምሮ ያለ ማዛዣ ሰዎችን ማሰር፣ ሃሳብን የመግለፅ ነፃነቶችን መገደብ፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን መከልከልና የሰዓት ዕላፊ አዋጅ መደንገግ ይገኙበታል።

ይህ አዋጅ በዚህ መልኩ ሥራ ላይ ከዋለ ችግሩን ያባብሳል፤ የፖለቲካ ቀውሱንም አይፈታም፡፡

የፖለቲካ ዴሞክራሲያዊነትና ሃሳብን በነፃነት መግለፅ አስፈላጊ ናቸው።

በመሆኑም የተቃዋሚ ሰልፈኞችንና በአጠቃላይም የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄ መፍታት አስፈላጊ ነው።

ለኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ያደረግነውን ጥሪ ዛሬም እንደግማለን።

ይህም ዜጎቹን እንዲያከብር፣ ህገ መንግሥቱ የሚፈቅድላቸውን ሃሳብን የመግለፅና የመደራጀት መብቶችን እንዲያከብር፣ እንዲሁም እነዚህን መብቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በመጠየቃቸው ያሠራቸውን እንዲፈታ እንጠይቃለን።

በነፃነት ትችት የሚያቀርቡትን ማፈንና ቁጥጥር ስር ማዋል በራስ ላይ ሽንፈትን ወይም ኪሳራን ከማስከተሉም በላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሚቀበሉት መፍትሄ ላይ እንዳይደረስም እንቅፋት ይሆናል።

በኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የሁከት አድራጎት እንዳይቀጥል ሁሉንም ወገኖች እናሳስባለን። ኢትዮጵያ አስተዳደሯን እንድታሻሻል፣ መፍትሔው ሰላማዊ ውይይት ነው።

ቁጥራቸው በጣም የበዛ ንጹሓን ዜጎች ህይወት ጠፍቷል፤ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።

ፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ ለፓርላማቸው ባሰሙት ንግግር አንዳንድ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለምሳሌም የመሬት ይዞታ መብትን፣ የምርጫ ህጎችን ማሻሻል፣ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ጥቅም እንዳለው መጥቀሳቸውን እንደግፋለን።

መንግሥት እነዚህን ሃሳቦች በፍጥነት በሥራ እንዲተረጉም እንዲሁም የፖለቲካ ምኅዳሩን በማስፋት ህገ-መንግሥቱ የሚፈቅዳቸውን መሠረታዊ መብቶች ለሕዝቡ እንዲመልስ እንጠይቃለን።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሕዝብን መብት የበለጠ አይጨፈልቅም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩትን አጢነናል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ የሰጡት መግለጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:22 0:00

XS
SM
MD
LG