በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዲሞክራቶች ትንቅንቅ - ዙር ሦስት


ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር በሚያክሄዱት ዘመቻ ቀዳሚ ቦታ ላይ ያሉት 10 ተወዳዳሪዎች ትናንት በተለያዩ ነጥቦች ላይ የሞቀ ክርክር አካሂደዋል። በመጪው ዓመት በሚደርገው ምርጫ ሊያሸንፏቸው የሚፈልጉትን ሪፖብሊካዊ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን ክፉኛ ነቅፈዋል።

ዓቃቤ ህግ የነበሩት የካሊፎርኒያ ሴኔተር ካሚላ ሀሪስ ትረምፕ የጥላቻና የማስፈራራት ተግባር ይፈፅማሉ በማለት ነቀፉ። በሁለት ዓመታት ተኩል የፕሬዚዳንትነት ጊዚያቸው ወቅት 12 ሺህ የሚሆኑ ውሸቶች ተናግረዋል ብለዋል።

ከሦስት ዓመታት በፊት ያካሄዱት የምርጫ ዘመቻቸው ከሩስያ ጋር ግንኙነት ይኖረው እንደሆነ ለማጣራት የተደረገውን የምርመራ ሂደት ለማሰናከል በመሞከር ተግባር ያልተከሰሱት “ሥልጣን ላይ ያለ ፕሬዚዳንት አይከሰስም” የሚል የፍርድ ሚኒስቴር ፖሊሲ ሥላለ ነው ብለዋል ሀሪስ። አያይዘውም “የአሜሪካ ህዝብ ክፉኛ መሮታል” ሲሉ አስገንዝበዋል።

ቴክሳስ ክፍለ ግዛትን ወክለው የምክር ቤት አባል የነበሩት /Beto 0’Rourke/ በበኩልቸው ኤል ፓሶ በተባለችው የክፍለ ግዛቲቱ ከተማ አንድ ሰው ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ የሜክሲኮ ተወላጆችን ዒላማ በማድረግ 22 ሰዎችን የገደለው “በፕሬዚዳንታችን ለመግደል ተነሳስቶ ነው” ብለዋል።

የሚኒሶታ ሴኔተር ኤሚ ክሎባሸር ደግሞ ትረምፕ “ከመምራት ይልቅ መዋሸት ይቀናቸዋል” ብለዋል። በውድድሩ ቀዳሚ ቦታ የያዙት የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ሴኔተሮች ኤልዝበት ዋረንና በርኒ ሳንደርስም በፕሬዚዳንት ትረምፕ ላይ የሰላ ነቀፊታ አስምተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG