በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ልዑክ በኒዤር የሦስት ቀናት ቆይታ አደረገ


ፎቶ ፋይል፦ አሜሪካ የውጪ ጉዳይ ምኒስቴር፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ሞሊ ፊ
ፎቶ ፋይል፦ አሜሪካ የውጪ ጉዳይ ምኒስቴር፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ሞሊ ፊ

የአሜሪካ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኒዤር የሦስት ቀናት ቆይታ በማድረግ፣ በዛች አገር በምርጫ ሥልጣን ይዘው የነበሩትን ፕሬዚደንት ሞሃመድ ባዙምን ካሰወገደው ሁንታ ጋራ ግንኙነት በሚታደስበት ሁኔታ ላይ ተወያይቷል ተብሏል።

የአሜሪካው ልዑክ ጉብኝት ያደረገው፣ ሁንታው ወደ ሥልጣን ከወጣ በኋላ አገሪቱ ወደ ሩሲያ በማዘመም ላይ ባለችበት ወቅት ነው ተብሏል።

የአሜሪካው ልዑክ፣ ጠቅላይ ምኒስትር አሊ ዘይንን ጨምሮ ከሌሎች የኒዤር ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋራ መወያየቱን አንድ ዲፕሎማሲያዊ ምንጭ ተናግረዋል ሲል ኤኤፍፒ በዘገባው አመልክቷል።

በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ምኒስቴር፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ሞሊ ፊ የተመራው ቡድን፣ በኒዤር ለሁለት ቀናት ለመቆየት ዕቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ለተጨማሪ አንድ ቀን መቆየቱን የኒዤር መንግሥታዊ ምንጮች አስታውቀዋል።

አሜሪካ፤ በኒዤር፣ በመቶ ሚሊዮን ዶላር በተገነባውና በበረሃማ አካባቢ በሚገኝ አንድ የድሮን ጣቢያ 1ሺሕ የሚሆኑ ወታደሮች አሏት፡፡ መፈንቅለ መንግሥቱ ተከትሎ የወታደሮቹ እንቅስቃሴ ተገድቧል። የአሜሪካ መንግሥትም ለኒዤር መንግሥት ሲሰጥ የነበረውን ርዳታ አቋርጧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG