በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ሳውዲ ያቀናው የዩናይትድ ስቴትስ ልኡካን ቡድን ተልዕኮውን አቋርጦ ተመለሰ


ፎቶ ፋይል፦ አይሁዳዊው የኦርቶዶክስ ቄስ አብርሃም ኩፐር ሐሙስ ከከተማው አዳራሽ ውጭ በሲቪክ እና እምነት መሪዎች ፊት ለፊት ንግግር እያደረጉ እአአ ግንቦት 20/202
ፎቶ ፋይል፦ አይሁዳዊው የኦርቶዶክስ ቄስ አብርሃም ኩፐር ሐሙስ ከከተማው አዳራሽ ውጭ በሲቪክ እና እምነት መሪዎች ፊት ለፊት ንግግር እያደረጉ እአአ ግንቦት 20/202

ከአባላቱ አንዱ ‘ኪፓ’ በመባል የሚታወቀውን የአይሁድ ሃይማኖት መለያ አነስተኛ ኮፊያቸውን እንዲያወልቁ መጠየቃቸውን ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ የሃይማኖት ነፃነት የተባለው መንግስታዊ አካል የልዑካን ቡድን የሥራ ጉብኝቱን አቋርጦ ለመመለስ መገደዱን ትናንት አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር አይሁዳዊው የኦርቶዶክስ ቄስ አብርሃም ኩፐር ያደረጉትን የሃይማኖት ኮፊያ እዲያወልቁ በተጠየቁበት እና ጥያቄውንም እንደማይቀበሉ ባሳወቁበት ወቅት፡ የልዑካን ቡድኑ ሪያድ አቅራቢያ የምትገኘውን እና በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበችውን፡ ታሪካዊ ከተማ ዲሪያ’ን በመጎብኘት ላይ እንደነበር ጨምሮ ገልጧል።

"ማንም ቢሆን ታሪካዊ ቦታዎችን መጎብኘት መከልከል የለበትም” ያሉት ኩፐር በመግለጫቸው “በተለይም አንድነት እና መሻሻልን፣ እንዲሁም እንደ አይሁድ መኖር መቻልን ለማንጸባረቅ፡ የታለመ ሲሆን” ብለዋል።

ኩፐር እና ምክትላቸው ቄስ ፍሬድሪክ ዴቪ ወደ አካባቢው ተጉዘው ይፋ ጉብኝት እንዲያደርጉ የተጋበዙት ባለፈው ማክሰኞ እንደነበር እና ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ ወደ ሌላ ጊዜ ሲተላለፍ መቆየቱንም ኮምሽኑ አመልክቷል። ይሁንና ጉብኝቱ ምንም እንኳን የሳውዲ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያመቻቸው ቢሆንም፤ ኩፐር በጉብኝቱ ሥፍራ እስካሉ እና በማንውም በአደባባይ በሚሆኑበት ወቅት ሃይማኖታዊ ኮፊያቸውን እንዲያወልቁ ባለስልጣናቱ እንደጠየቋቸው ጠቁሟል።

“ሳውዲ አረቢያ ለ2030 በያዘችው ራዕይ መሰረት አበረታች ለውጦችን በማድረግ ላይ ትገኛለች” ያሉት ኩፐር "ይሁን እንጂ፣ በተለይ ጸረ ሴማዊ አዝማሚያዎች በተበራከቱበት በአሁኑ ወቅት፣ ሃይማኖታዊ አለባበሴን እንድቀይር በመጠየቄ ጉብኝታችንን ልናቋርጥ ተገደል" ብለዋል።

ኮሚሽኑ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስትን እንዲያማክር በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የተሰመ አካል ነው።

ድንገቱ የተዘገበው የጋዛውን ጦርነት ተከትሎ በሳዑዲ አረቢያ እና የዩናይትድ ስቴትስ አጋር በሆነችው እስራኤል መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እና ግጭቱም እንዳበቃ ዩናይትድ ስቴትስ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመቀየር የምታደርገውን ጥረት እያውጠነጠነች ባለችበት ወቅት ነው።

ዋሽንግተን የሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ዜና ዘገባውን ባቀረበው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ለቀረበለት ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG