በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መከላከያ ሚኒስትር ጄምስ ማቲስ ሥራ ሊለቁ ነው

ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጄምስ ማቲስ
ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጄምስ ማቲስ

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጄምስ ማቲስ በመጪው የካቲት ወር ላይ ሥራቸውን እንደሚለቁ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ትላንት ከሰዓት በኋላ አስታውቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጄምስ ማቲስ በመጪው የካቲት ወር ላይ ሥራቸውን እንደሚለቁ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ትላንት ከሰዓት በኋላ አስታውቀዋል።

“ጄኔራል ማቲስ በአስተዳደሬ ሥር ለሁለት ዓመታት ያህል በመከላከይ ሚኒስትርነት ካገለገሉ በኋላ፣ በክብር ጡረታ ይወጣሉ” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ በትዊተር አስታውቀዋል።

“በጄነራል ማቲስ የሥራ ወቅት ብዙ ትልልቅ ሥራዎች ተሰርተዋል። በተለይም አዳዲስ የውጊያ ዕቃዎችን በመግዛት ረገድ” ሲሉም ፕሬዚዳንቱ አክለዋል። ለአገልግሎታቸው አመሰግናለሁ ካሉ በኋላ በቅርቡ አዲስ መከላከያ ሚኒስትር እንደሚሾም አውስተዋል።

የመከላከያው ሚኒስትር ሥራ እንደሚለቁ የተነገረው የአሜሪካ ወታደሮች ከሶርያ እንደሚወጡ ትረምፕ በተናገሩ ማግሥት ነው። የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር የአሜሪካ ወታደሮችን ከሶርያ መውጣት ይቃወማል።

ፕሬዚዳንቱ ማቲስ ጡረታ ይወጣሉ ቢሉም ጄኔራል ማቲስ በመሥርያ ቤታቸው ይፋ ያደረጉት ደብዳቤ ግን በራሳቸው እየለቀቁ መሆናቸውን ይገልጻል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG