በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ሩሲያ ባኽሙትን ብትይዝ ስትራተጂያው ለውጥ እንደማያመጣ የዩስ የመከላከያ ሚንስትር ተናገሩ

ሩሲያ ባኽሙትን ብትይዝ ስትራተጂያው ለውጥ እንደማያመጣ የዩስ የመከላከያ ሚንስትር ተናገሩ


የዩክሬን ኅይሎች መስመር ባኻሙት ከተማ ወጣ ብሎ ባለ ሥፍራ
የዩክሬን ኅይሎች መስመር ባኻሙት ከተማ ወጣ ብሎ ባለ ሥፍራ

የሩሲያ ወታደሮች የምስራቅ ዩክሬኗን ባኻሙት ከተማ ቢይዟት በጦርነቱ ይዞታ ወሳኝ ለውጥ አያመጣም ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ተናገሩ፡፡

የመከላከያ ሚንስትሩ በዮርዳኖስ ጉብኝታቸው ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል የባኽሙት መያዝ አንድምታው “ከስትራተጂያዊ ይልቅ ተምሳሌታዊነቱ ይበልጣል” ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡

የሩሲያ ኅይሎች የዩክሬን ዶኔትስክ ክፍለ ግዛት የምትገኘውን ባኽሙትን ለመያዝ እየሞከሩ ሲሆን ለወራት ከባድ ውጊያ ሲካሂድ ቆይቷል፡፡ ዩክሬን ወታደሮቿን ከከተማዋ በስተምዕራብ አካባቢ አቅጣጫ እንዲያመሩ ያደረገው ውሳኔ ስትራተጂያዊ ድክመት አድርገው እንደማይመለከቱት የመከላከያ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የጦርነት ጥናት ተቋም የተባለ ዋሽንግተን የሚገኝ የምርምር ተቋም የዩክሬን ወታደሮች ከባኽሙት ታክቲካዊ የማፈግፈግ ዕርምጃ የወሰዱ እንደሚመስል ተናግሯል፡፡ ሆኖም ሙሉ በሙሉ ለቅቀው ለመውጣት እየተንቀሳቀሱ ነው የሚል ድምዳሜ ከወዲሁ ለመስጠት እንደማይቻል አክሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትሯ ሴርጌይ ሾይጉ ደቡባዊ ዩክሬን የሚገኙ ወታደሮችን እና ሀኪም ቤት መጎብኘታቸውን አመልክታለች፡፡

XS
SM
MD
LG