በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የኮቪድ-19 ቫይረስ ከቻይና ላብራቶሪ አፈትልኮ የወጣ ነው” ኤፍቢአይ


የኮቪድ-19 ወረርሽን በቻይና ዉሃን ከሚገኝ ላብራቶሪ አፈትልኮ የወጣ መሆኑን አሜሪካ ታምናለች ሲሉ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ዲሬክተር ክሪስቶፈር ሬይ ይፋ አድርገዋል፡፡ ህኖም ግን በዚህ ድምዳሜ ላይ በተለያዩ የአሜሪካ መረጃ ተቋማት መካከል ልዩነት አለ ተብሏል፡፡

ዋይት ሃውስ የኤፍቢአይን ግኝት ተናንት ረቡዕ አጣጥሏል ስትል የቪኦኤ የም/ቤት ዘጋቢ ካትሪን ጊብሰን ባጠናቀረችው ዘገባ አመልክታለች፡፡

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርም በአገሪቱ የመረጃ ተቋማት መካከል በጉዳዩ ላይ ልዩነት እንዳለ አስታውቋል፡፡

የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በበኩላቸው ከአሜሪካ የተሰማው መደምደሚያ ተአማኒነት የሚጎድለው ነው ብለዋል፡፡

የኮቪድ-19 መነሻ የት ነው የሚለው ጥያቄ አሜሪካ በዚህ ሳምንት የጀመረችውና አገሪቱ ከቻይና ጋር የነበራትን ፉክክር የሚመረምረው የሁለት ዓመት ፕሮጀክት ዋናው ትኩረት የሆናል ተብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG