በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዩናይትድ ስቴትስ


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ተያዥች ቁጥር 3,774,769 መድረሱን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል አስታውቋል። ከበሽታው ያገገሙ 1,131,121 ሲሆኑ የሞቱ ደግሞ 140,541 ናቸው።

ቫይረሱ በፍጥነት እየተዛመተባቸው ካሉት የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች አንዷ የሆነችው ፍሎሪዳ አርባ አምስት ሆስፒታሎች አንድም ክፍት የፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል አልጋ እንደሌላቸው አስታውቋል።

ፍሎሪዳ ውስጥ ትናንት ዕሁድ ብቻ 12ሽህ አዲስ የቫይረሱ ተግላጮች ተገኝተዋል፤ በቀን ከአሥር ሺህ በላይ ሲመዘገብ የትናንቱ አምስተኛ አከታታይ ቀን ነው።

በዓለም ዙሪያ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት ሰዎች ቁጥር 14,535,008 በበሽታውም ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉት ቁጥር 606,810 መድረሱንም የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል መረጃ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG