ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች የመን ውስጥ በሚንቀሳቀሱ በአልቃይዳ እና በእስላማዊ መንግሥት ላይ የአየር ድብደባቸውን እፋፍመው ቀጥለዋል። ባለፉት ታኅሣሥና ጥር ወራት ውስጥ አሥራ ሥምንት የአየር ጥቃቶችን ማካሄዳቸው ተዘግቧል።
አብዛኛው ጥቃት ዒላማ ያደረገው አልቃይዳን ሲሆን አምስቱ ጥቃቶች ብቻ እስላማዊ መንግሥት ላይ ያነጣጠሩ እንደነበሩ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ አረግግጠዋል።
ባለፈው ታኅሣሥወር ከተካሄዱት ጥቃቶች አንዱ የዓረቡ ሰላጤ አልቃይዳ የተባለው ቡድን በማሪብ ክፍለ ግዛት የጦር መሳሪያ አቅርቦት ኃላፊ የነበረውን ሃቢብ አልሳናኒን መግደሉን የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል ዛሬ አስታውቋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ