በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቲክ ቶክ ከቻይና ቁጥጥር ካልተላቀቀ በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዳይውል በተወካዮች ምክር ቤት ሕግ ፀደቀ


ቲክ ቶክ
ቲክ ቶክ

ቲክ ቶክ ከቻይናው እናት ኩባንያ ባይት ዳንስ ቁጥጥር ካልተላቀቀ ወይም ለዩናይትድ ስቴትስ የሚጠቀምበት ሶፍትዌር ለሌላ ወገን ካልተሸጠ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚከለክል ሕግ በተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ረቡዕ ፀድቋል።

በሁለቱ ፓርቲዎች በጋራ የወጣው ሕግ የቲክ ቶክ ኩባንያ በአሜሪካ ጥቅም ላይ ለመዋል “የውጪ ተቀናቃኝ” ተብሎ ከተገለፀው ከእናት ኩባንያው ከባይት ዳንስ እንዲላቀቅ የስድስት ወራት ጊዜ ሰጥቶታል።

“ቲክ ቶክ ማድረግ ያለበት ከቻይና ኮሚኒስት ፖርቲ ቁጥጥር ራሱን ማላቀቅ ነው። ያን የማያደርግ ከሆነ ግን በአሜሪካ የመተግበሪያ ገበያ ላይ አይቀርብም” ሲሉ ሕግ አውጪዎቹ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ቲክ ቶክ የሰበሰበውን መረጃ ለቻይና መንግሥት ሊያስተላልፍ ይችላል የሚል ስጋት የአሜሪካ ሕግ አውጪዎችን ሲያስጨንቃቸው ከርሟል።

ሕጉ በመቀጠል በዲሞክራቶቹ ቁጥጥር ሥር ወዳለው የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ወይም ሴኔት የሚላክ ሲሆን፣ በዛም ጠንከር ያለ ሙግት ሊገጥመው እንደሚችል ተነግሯል። አንዳንድ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የዲሞክራቲክ ፓርቲው አባላት፣ አንድን መተግበሪያ ኢላማ ያደረገ ሕግ የማውጣቱን ሕጋዊነት በተመለከተ ጥርጣሬ አላቸው ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG