በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቲክቶክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሜሪካ ኮንግረስ ቀረቡ


የቲክቶክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾው ዜ ቺው
የቲክቶክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾው ዜ ቺው

የመረጃና የግለሰቦች ደህንነትን በተመለከተ ከፍተኛ ትችት የሚቀርብበት የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ የሆነው ቲክቶክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መተግበሪያው ለምን መታገድ እንደሌለበት በአሜሪካ ኮንግረስ ቀርበው አስረድተዋል፡፡

150 ሚሊዮን አሜሪካውያን የሚጠቀሙት የቲክቶክ መተግበሪያ የመረጃ አያያዝና የተጠቃሚዎች ደህነንት ጉዳይ የአሜሪካ ባልሥልጣናትን አሳስቧል።

በዓለም የፖለቲካ ግኑኝነት ፍጥጫ ላይ የሚገኙት ቻይናና አሜሪካ መሃል፣ ቲክቶክና ባይት ዳንስ የተባለው የቻይና እናት ኩባንያው አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል።

ሥራ አስፈጻሚው ሾው ዜ ቺው ከአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን አስተናግደዋል።

ኩባንያው ከቤጂንግ ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለው በሚል፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለወጣት ተጠቃሚዎች ደህንነት እንዲሁም ለአገሪቱም ደህንነት አደገኛ ነው ሲሉ ይከራክራሉ፡፡

የተጠቃሚዎች የግል መረጃ የቻይና መንግሥት እጅ ይወድቃል ወይም የአገሪቱ ኮሚኒስት ፓርቲ የፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ ይሆናል ሲሉ አሜሪካውያኑ ይሰጋሉ።

XS
SM
MD
LG