ቲክ ቶክ፤ በቻይና መንግስት ቁጥጥር ሥር እንደሆነ ከሚነገረው እናት ኩባንያው ባይት ዳንስ ካልተላቀቀ፣ መተገበሪያው በአሜሪካ ጥቅም እንዳይውል የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ም/ቤት ትናንት ረቡዕ አንድ ሕግ ማውጣቱን ተከትሉ፣ የቻይና መንግስት ቁጣውን አሰምቷል።
በሌላ በኩል ደግሞ ትናንት በተወካዮች ም/ቤት የፀደቀው ሕግ የንግግር ነፃነትን የሚገድብ ነው በሚል በሕግ አውጪው ሸንጎ ወይም ሴኔት ላይፀድቅ ይችላል ተብሏል።
ከቪኦኤዋ የኮንግረስ ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን እንዲሁም ከአሶስዬትድ ፕረስ ያገኘነውን ዘገባዎች ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም