በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የተኩስ ማቆም ስምምነት እንደሚደረግ አሜሪካ ተስፋ አላት


በሱዳን የተኩስ ማቆም ስምምነት እንደሚደረግ አሜሪካ ተስፋ አላት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:15 0:00

በሱዳን የተኩስ ማቆም ስምምነት እንደሚደረግ አሜሪካ ተስፋ አላት

በጀዳ ሳዑዲ አረቢያ በመነጋገር ላይ ያሉት ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች፣ ሰብአዊ አገልግሎትን ለማዳረስ እንዲቻል፣ ጊዜያዊ የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ ይደርሳሉ፤ የሚል ጥንቃቄ የተሞላበት ተስፋ እንዳላቸው፣ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች፣ ትላንት ረቡዕ ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ወር ሚያዝያ ሰባት በተቀሰቀሰውና አራተኛ ሳምንቱን በአስቆጠረው ውጊያ፣ እስከ አሁን 750 ሰዎች ሲገደሉ፣ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡

በሱዳን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጀነራል አብዱል ፋታሕ አል ቡርሃንና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዥ ጀነራል ሞሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ተወካዮች መካከል፣ በጀዳ ሳዑዲ አረቢያ እየተካሔደ ያለው የሰላም ንግግር፣ ተስፋ የሚሰጥ ነው፤ እየተባለ ባለበትም ሰዓት፣ በካርቱም የተኩስ ድምፆች በመሰማት ላይ ናቸው፡፡

ጥንቃቄ የተሞላበት ተስፋቸውን የገለጹልኝን የእኛን አደራዳሪዎች አነጋግሬያለኹ፡፡ ንግግሩ አሁን ባለበት ደረጃ ስኬታማ ከኾነ፣ የሱዳን ሕዝብ ለዓመታት ሲጠይቅ የነበረውን በሲቪል የሚመራ መንግሥት ለመመሥረት እንዲቻል፣ ቋሚ የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ ተደርሶ፤ የአገር ውስጥ፣ የቀጣናው እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ አካላት የሚሳተፉበት፣ ሰፋ ያለ ውይይት ለማድረግ ያስችላል፤”

“ጥንቃቄ የተሞላበት ተስፋቸውን የገለጹልኝን የእኛን አደራዳሪዎች አነጋግሬያለኹ፡፡ ንግግሩ አሁን ባለበት ደረጃ ስኬታማ ከኾነ፣ የሱዳን ሕዝብ ለዓመታት ሲጠይቅ የነበረውን በሲቪል የሚመራ መንግሥት ለመመሥረት እንዲቻል፣ ቋሚ የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ ተደርሶ፤ የአገር ውስጥ፣ የቀጣናው እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ አካላት የሚሳተፉበት፣ ሰፋ ያለ ውይይት ለማድረግ ያስችላል፤” ሲሉ፣ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ሓላፊ ቪክቶሪያ ኑላንድ አብራርተዋል፡፡

ቡርሃን፣ ከሁለት ዓመታት በፊት፣ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ የተደረገውን ወታደራዊ ሥዒረ መንግሥት መርተዋል፡፡ “አሜሪካ፣በዚያ መፈንቅለ መንግሥት ላይ ተገቢውን አቋም አልያዘችበትም፤” ሲሉ፣ የሕግ አውጪው ም/ቤት አባላት ተችተዋል፡፡

“ማዕቀብ መጣል ሲገባን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሱዳናውያንን የዴሞክራሲ ተስፋ፣ በከፋ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና ዘረፋ፣ ተጠያቂ እና ተባባሪ በኾኑት ሁለቱ ተቀናቃኝ ጀነራሎች እጅ ጣልነው፤” ሲሉ የተናገሩት፣ በም/ቤቱ የውጭ ግንኙነት ሊቀ መንበር ሴናተር ባብ ሜኔንዴዝ ናቸው፡፡

ሱዳን በዚኽ ወቅት፣ ወደ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት መሸጋገር ነበረባት፡፡ ግጭቱ ያን አጨናግፏል፡፡ የባይደን አስተዳደር፣ አሁንም ሱዳንን በተመለከተ ግልጽ ስትራቴጂ የለውም፤ ሲሉ፣ አንዳንድ የሪፐብሊካን ም/ቤት አባላት ይናገራሉ፡፡

“አስተዳደሩ ለሱዳን ያለውን ርእይ በግልጽ እንዲያስቀምጥ ጠይቄያለኹ፡፡ አሁንም መልስ እየጠበቅኹ ነው፤” ያሉት ሴናተር ጂም ሪሽ ናቸው፡፡ ሱዳንን የሚያውኩ ባላቸው ግለሰቦች ላይ፣ ማዕቀብ እንዲጣል ዋይት ሓውስ፣ ባለፈው ሳምንት ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡

ሌላው ሴናተር፣ ዴሞክራቱ ክሪስ ቫን ሆለን፣ በመካሔድ ላይ ያለው ንግግር፣ ግልጽ ግብ ያለው ነው፤ ይላሉ፡፡

የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲኖር እንሻለን፡፡ ለድርድር ጊዜ ለመስጠት፣ የተኩስ ማቆም ስምምነቱ እንዲዘልቅ እንፈልጋለን፡፡ በርግጥ የመጨረሻ ግቡ፣ አገሪቱን፣ የሱዳን ሕዝብ መሻቱን ወደሚገልጽበት የዴሞክራሲ ጎዳና መመለስ ነው፤”

“የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲኖር እንሻለን፡፡ ለድርድር ጊዜ ለመስጠት፣ የተኩስ ማቆም ስምምነቱ እንዲዘልቅ እንፈልጋለን፡፡ በርግጥ የመጨረሻ ግቡ፣ አገሪቱን፣ የሱዳን ሕዝብ መሻቱን ወደሚገልጽበት የዴሞክራሲ ጎዳና መመለስ ነው፤” ብለዋል ቫን ሆለን፡፡

ከግጭቱም በፊት ቢኾን፣ ከሱዳን ሕዝብ ሦስት እጅ የሚኾነው፣ ሰብአዊ ርዳታ የሚያስፈልገው የነበረ ነው፡፡ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚለው ደግሞ፣ ኹኔታው አሁን ይበልጥ ከፍቷል፡፡

“በአገር ውስጥ፣ ከ700 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ ከ170 ሺሕ በላይ ደግሞ፣ ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰድደዋል፡፡ የግጭቱ ተጋቦት፣ በሱዳን ድንበር ውስጥ ብቻ የታጠረ አይኾንም ማለት ነው፡፡ መዘዙ ቀጣናውንም ያካልላል፡፡ ወትሮውንም በበርካታ ሀገራት የነበረውን ሰብአዊ ቀውስ ያባብሳል፤” ብለዋል፣ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት(ዩኤስኤይድ) የሰብአዊ ርዳታ ሓላፊ የኾኑት ሳራ ቻርለስ፡፡

ሱዳን ውስጥ ከተመዘገቡት፣ አምስት ሺሕ አሜሪካውያን ውስጥ፣ 1ሺሕ 300 ያህሉን ከአገሪቱ እንዳስወጡ፣ የውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ ባለሥልጣናት ይናገራሉ፡፡ ቀሪዎቹም እዚያው ለመሰንበት መምረጣቸውን አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG