በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጆርጅያው ተወካይ አፈ ጉባኤውን ከወንበራቸው ለማንሳት ዝተዋል


በአሜሪካ የተወካዮች ም/ቤት አባሏና የጆርጅያ የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይዋ ማርጀሪ ቴይለር ግሪን
በአሜሪካ የተወካዮች ም/ቤት አባሏና የጆርጅያ የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይዋ ማርጀሪ ቴይለር ግሪን

በአሜሪካ የተወካዮች ም/ቤት አባሏና የጆርጅያ የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይዋ ማርጀሪ ቴይለር ግሪን፣ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የሆኑትን ማይክ ጀንሰን ከወንበራቸው ለማንሳት ድምፅ እንዲሰጥ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።

የዲሞክራቲክ ፓርቲው አባላት ማይክ ጀንሰንን እንደሚታደጉ ማስታወቃቸውን ተከትሎ፣ ተወካይዋ የሪፐብሊካን ፓርቲ ጓዶቻቸው ወገናቸውን እንዲለዩ በማስገደድ ላይ ናቸው።

በካፒቶል ደጃፍ ላይ ሆነው ዛሬ የተናገሩት ማርጀሪ ቴይለር ግሪን፣ የህዳር ወሩ ምርጫ በተቃረበበት በዚህ ወቅት፣ በፓርቲው ውስጥ ፍትጊያ ከመፍጠር እንዲታቀቡ ከቀድሞው ፕሬዝደትን ዶናልድ ትረም ጭምር የተነገራቸው ቢሆንም የሚቀበሉት አልሆነም።

ሪፐብሊካኑ አፈ ጉባኤ ማይክ ጀንሰን ከዲሞክራቶች ጋራ በመተባበር የሃገሪቱን በጀትና ለዩክሬን እንዲሁም ለሌሎችም የአሜሪካ ሸሪኮች የሚሰጠው የበጀት ሕግ እንዲፀድቅ በማድረጋቸው፣ በአንዳንድ የፓርቲያቸው ሰዎች ጥርስ ተነክሶባቸዋል። ዲሞክራቶቹ አፈ ጉባኤው ከሚመጣባቸው ማንኛውም አደጋ በድምጻቸው እንደሚታደጉ በማስታወቅ ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG