በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሪፐብሊካኑ ወደ አራተኛው ቀን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ምርጫ ድርድር ገቡ


የካሊፎኒያ የህዝብ እንደራሴ ኬቪን ማካርቲን
የካሊፎኒያ የህዝብ እንደራሴ ኬቪን ማካርቲን

ሪፐብሊካኑ የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት አዲሱን አፈ ጉባኤያቸውን ለመምረጥ የአራተኛ ቀን ሙከራቸውን ዛሬ ዓርብ ያደርጋሉ፡፡

የካሊፎኒያውን የህዝብ እንደራሴ ኬቪን ማካርቲን የወግ አጣባቂ እሴቶችን ለማስጠበቅ በቂ አይደሉም ብለው የሚያምኑት 20 የሚሆኑ ወግ አጥባቂ የፓርቲው አባላት የአፈ ጉባኤውን ምርጫ ለሦስት ቀናት በተሳካ ሁኔታ አግደውት ቆይተዋል፡፡

435 አባላት ያሉት የህዝብ ተወካዮቹ ምክር ቤት ለ16 ዓመታት የህዝብ እንደራሴና አሁን በምክር ቤቱ የሪፐብሊካን መሪ የሆኑት መካርቲን ለመምረጥ የሚያስፈልገውን 218 ድምጽ የጎደሉትን ጥቂት ድምጾች ማግኘት አቅቶታል፡፡

ሌሊቱን ድርድር ቢደረግም በጠባብ የድምጽ ብልጫ አብላጫውን የምክር ቤት መቀመጫዎችን የያዙት ሪፐብሊካኖች ሪፐብሊካኑን ኬቭን ማካርቲ በአፈ ጉባኤነት ለመምረጥ የሚያስፈልጉትን ጥቂት ድምጾች መንፈጉን ቀጥለዋል።

በዚህ የተነሳም በሦስቱ ቀናት ለ10ኛው ዙር የተደረገው ምርጫ ለመሳካቱ ምርክ ቤቱ ድምጽ የመሰጠቱ ሂደት እስከ አርብ እኩለ ቀን ድረስ እንዲቆይ ድምጽ ሰጥቷል፡፡

አፈ ጉባኤ መካርቲ ከአፈ ጉባኤነቱ ዕጩነት ራሳቸው እንደሚያገልሉ እስካሁን ምንም ዓይነት ፍንጭ አልሰጡም፡፡

XS
SM
MD
LG