በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በእስራኤል ጉዳይ ተከፋፍለዋል


የእስራኤልና ፍልስጤማውያን ግጭት
የእስራኤልና ፍልስጤማውያን ግጭት
የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በእስራኤል ጉዳይ ተከፋፍለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00

የእስራኤልና ፍልስጤማውያን ግጭት ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ባላሳየበት በአሁኑ ሰዓት፣ ዴሞክራቶቹ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት፣ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች ግን፣ የሀማስን ጥቃት በማውገዝ፣ “በሁለቱ ወገኖች ድርጊት መካከል እኩል የሆነ የሞራል ተጠያቂነት የለም” ብለዋል፡፡

ላላፉት 10 ቀናት በመካሄድ ላይ ባለው የእስራኤል እና የፍልስጤማውያን ግጭት ጉዳይ ላይ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ህግ አውጭዎች ተከፋፍለዋል፡፡

እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው፣ የእስራኤል ኤምባሲ ፊለት ለፊትም የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡

እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምታደርሰው የሰብአዊ መብት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት የሚሉት የሀማስ ተዋጊዎች ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ሲተኩሱ እስራኤልም በምላሹ ጋዛን በአየር ጥቃት ደብድባለች፡፡

ዴሞክራቱ ሴንተር ክሪስ መርፊ ይህን ብለዋል።

እስራኤላውያኑ የወደፊቱን የፍልስጤማውያንን ግዛት እንዳይመሰረት ለማድረግ ሆን ብለው ማፈናቀልና ሰፈራን እንደ ስልት መጠቀማቸው ስህተት ነው፡፡ ይህ ፖሊሲ፣ ምናልባት ለናታኒያሁ የጥምር መንግሥት ፖለቲካቸው ህብረት ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ በፍልስጤማውያን ዘንድ ግን፣ መጭውን አስመልከቶ ያደረባቸውን ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይበልጥ እያበረታቱ ነው፡፡ የፍስልጤም መሪዎችም ሥልጣን ላይ ለመቆየት ጸረ እስራኤል እና ጸረ ሴማውያን ቅሰቀሳቸውን እንደ ዋና መሰሪያቸው መጠቀማቸው ስህተት ነው፡፡

ከዴሞክራቶቹ ተራማጅ አቋም ያላቸው፣ እንደ ሴነተር በርኒ ሳንደርስ እና የተወካዮች ምክር ቤቷ አባል አሌክዛንደር ኦካሲዮ ኮርቴዝ፣ የመሳሰሉት፣ በእስራኤል የአየር ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰላማዊ ዜጎች ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኤል የምትሰጠውን እርዳታ መልሳ እንድትመረምር ጠይቀዋል፡፡

መካከለኛ አቋም ያላቸው አብዛኞቹ አባላት ግን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ዴሞክራቱ ሴነተር ባብ መንዴዝ እንዲህ ብለዋል

“የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊነክን እና ፕሬዚዳንት ባይደን ራሳቸው ከበሰተኋላ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ በቀጥታ ከእስራኤል መንግሥት እንዲሁም ከግብጽ እና በአካባቢው ካሉ አጋር አገሮች ጋር በመተባበር ግጭቱ እንዲቆም እየሠሩ ነው፡፡”

እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት 217 ፍልስጤማውያንን ስትገድል፣ የፍልስጤም ተፋላሚዎች ደግሞ በተኮሷቸው ሮኬቶች፣ 12 እስራኤላውያን ሞተዋል፡፡

የሪፐብሊካን ፓርቲ የምክር ቤት አባላት፣ ሁለቱም ወገኖች እኩል ተጠያቂ አይደሉም ይላሉ፡፡ የመወሰኛው ምክር ቤት የሪፐብሊካን አባላት መሪ ሚች መካኔል እንዲህ ብለዋል

“እስራኤልን ከአደጋ ላይ ስትወድቅ ዝም ብለው ማየት የሚፈልጉ ጥቂት ያልሆነ ቁጥር ያላቸው ዴሞክራቶች አሉ፡፡ እዚህ ላይም በኩል ዓይን የሚታይ ነገር ያለም ያስመስላሉ፡፡ ምንም ዓይነት የሞራል እኩልነት የለም፡፡ በአንድ በኩል ያሉት አሸባሪዎች አሉ፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህ ፍልስጥሜውያንን ራሳቸውን እያሳሳቱና ራሳቸውን አደጋ ላይ እንዲጥሉ እየገፋፉ ነው፡፡ እስራኤሎች ደግሞ አገራቸውን ለመከላከል ሲሉ በሚወስዱት እምርጃ ኢላማቸውን በጥንቃቄ ለመምታት ከመንገዳቸው እንዲወጡ እየተደረጉ ነው፡፡”

የሰኔት ሪፐብሊካን አባላት፣ የባይደን አስተዳደር የኢራንን የኒኩዩለር ስምምነት በድጋሚ ለመፈጸም በወሰድ ላይ ያለውን እርምጃ በማውገዝ፣ እስራኤልን ለመከላከል ተጨማሪ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለበት ይናገራሉ፡፡

ሪፐብሊካኑ ሴንተር ቴድ ኩሩዝ እንዲህ ብለዋል

“የባይደን አስተዳደር እስራኤልን ከማብጠልጠልና ከማናናቅ ይልቅ፣ እንዲያውም የብዙ ሺ ሰዎችን ህይወት እያተረፈ የሚገኘውን “አይረን ዶም” የተባለውን የሮኬቶች ማምከኛ መሳሪያ፣ ጉድለት የምናሟለበትንና የምናጠናክርበትን መንገድ እንፈልጋለን ነው ማለት ያለበት፡፡”

ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ በአብዛኛው ስር የሰደደም ባይሆን፣ ለእስራኤል ሊሸጥ የታሰበውን፣ የ735 ሚሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነትን የተቃወሙ፣ ተራማጆቹ ዴሞክራት የምክር ቤት አባላት፣ የባይደን አስተዳደርን እንደተፈታተኑት ተመልክቷል፡፡ ስምምነቱ የተረፈው ለጥቂት መሆኑንም ተነግሯል፡፡

የቪኦኤ የምክር ቤት ዘጋቢ፣ ካትሪን ጊብሰን ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG