በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምክር ቤቱ ፖሊሶች “የመንፈንቀለ መንግስት ሙከራ ነበር!”


ጥር 6 በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ በተካሄደው አመጽ ቃላቸውን የሰጡት የፖሊስ መኮንን ስሜታዊ ነበሩ
ጥር 6 በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ በተካሄደው አመጽ ቃላቸውን የሰጡት የፖሊስ መኮንን ስሜታዊ ነበሩ

እ.ኤ.አ. የጥር 6 የ 2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤትን ለመቀልበስ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ደጋፊዎች የተፈጸሙትን ክስተቶች ለመመርመር የተሰየሙት ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ህግ አውጭዎች ባለፈው ማክሰኞ የአራት የህግ አሰባከባሪዎችን ስሜት የተሞላ ምስክርነት አድምጠዋል፡፡ የተሰየመው ኮሚቴ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በአመጹ ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎም እንደሚመረምር ተመልክቷል፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ደጋፊዎች የ2020ውን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስ የምክር ቤቱ ህንጻ ላይ ጥቃት ከፈጸሙ ወዲህ ባላፉት ስድስት ወራት ውስጥ የሪፐብሊካን አባላት በእለቱ የደረሰውን ከፍተኛ ጉዳት ሲያጣጥሉት ቆይተዋል፡፡

የምክር ቤቱ ጠባቂ የፖሊስ አባላት ግን ትናንት ማክሰኞ በሰጡት ቃል ይህን ውድቅ አድርገውታል፡፡ በምክር ቤቱ ፖሊስ የሆኑት አምሳ አለቃ አኩሊያኖ ጎኔል እንዲህ ይላሉ

“በዚያን ቀን በምክር ቤቱ ህንጻ ውስጥ እየተከተሰተ የነበረው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነበር፡፡ ሌላ አገር ቢሆን ኖሮ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፏን ትልክ ነበር፡፡”

የምክር ቤቱ ፖሊሶች “የነበረው የመንፈንቀለ መንግስት ሙከራ ነው!”
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00


ጎኔል በምክር ቤቱ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ደጋፊዎች በጭካኔ የተደበደቡ መሆናቸውን በመግለጽ የምስክርነት ቃላቸውን ከሰጡ አራት የህግ አስከባሪዎች መካከል አንደኛው ናቸው፡፡ሌላኛው መስካሪ በዋሽንግተን አካባቢ የፖሊስ መምሪያ አባል የሆኑት ማይክል ፋኖኔ ናቸው፡፡ እንዲህ ብለዋል

“ ወታደሮቹ በሰልፍ ከቆምንበት ነጥለው በመጎተት ወሰዱኝ፡፡ አንደኛው ከመካከላቸው “አንደኛውን አግኝቻለሁ” ብሎ ሲጮህ ሰምቸዋለሁ፡፡ በአመጸኞቹ መካከል ተይዥ እንደገባሁ ያንጠለጠልኩትን መታወቂያ መንጭቀው ወሰዱ፡፡ የመገናኛ ሬዲዮውን ነጠቁ፣ ላዬ ላይ በሚገባ ታስሮ የነበረውን ተቀጣጣይ መሳሪያ ወሰዱ፡፡ ከዚያ በኋላ በቡጢና ጠንካራ ብረት መስሎ በተሰማኝ ነገር ይደበድቡኝ ጀመር፡፡”

ጥቁሮችን የሚዘልፉ ያልተገባ ጸያፍ ቃል በመጠቀም ይራገሙና ይጮኹ የነበሩ ወደ 20 የሚሆኑ ሰዎችን የተቀላቀሉ ሌሎች ተሳታፊዎች እንደነበሩም በምስክርነት ከቀረቡት የፖሊሶች መኮንኖቹ አንዱ የሆኑት ሃሪ ዱን ተናግረዋል፡፡

በሁለት መቶ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በምክር ቤቱ ላይ ተቃጥቷል የተባለውን የከፋ አደጋ ምክንያት ለመመርመር በተቋቋመው ልዩ ኮሚቴ ፊት የተጀመረው የምስክርነት ቃል በስሜት የተሞላ እንደነበርም ተመልክቷል፡፡ ዴሞክራቱ የምክር ቤት አባል ቤኒ ቶምሰን እንዲህ ይላሉ

“በዚህ ምርመራ ፖለቲካ ወይም ትብብር ቦታ የላቸውም፡፡ ዋናው ኃላፊነታችን እውነታዎች ወዴት እንደሚመሩን መከተል ብቻ ነው፡፡”

ይሁን እንጂ በምክር ቤቱ ከፍተኛው የሪፐብሊካን ተወካይ ኬቭን መካርቲ እሳቸው ያቀረቧቸውን ሁለት የኮሚቴ አባላት ከኮሚቴው እንዲወገዱ መወሰናቸውን በመግለጽ፣ የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ናንሲ ፐሎሲን እንደሚከተለው ተችተዋል፡፡

“አፈጉባኤዋ ፐሎሲ ለኮሚቴው የሚመርጡት እሳቸው ብቻ የሚፈልትጉትን ጥያቄዎች ብቻ የሚጠይቁ ሰዎችን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ያ ኮሚቴ ተቀባይነት የሌለውና የሚያቀርበውም ሪፖርት ውድቅ የተደረገ ኮሚቴ ነው፡፡ ማንም ሊያምነው የማይችል ቅጥፈት ነው፡፡”

የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ትራምፕን በመቃወማቸው ከአመራር የተወገዱትን ሊዝ ቼኒን ጨምሮ በኮሚቴው ውስጥ የታቀፉ አባሎቻቸውን ሳይቀር እየተሟገቱ ነው፡፡ ቼኒ፣ ትራምፕ አመጹን በማነሳሳት የነበራቸው ትክክለኛ ድርሻ መመርመር አለበት ባይናቸው፡፡ እንዲህ ብለዋል

“ በዚያች እለት ዋይት ሐውስ ውስጥ በእያንዳንዷ ደቂቃ ምን እንደተከሰተ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ከጥቃቱ በፊትና በኋላ የነበረውን እያንዳንዱ ስልክ እያንዳንዱ ንግግር እያንዳንዱ ስብሰባ ማወቅ አለብን፡፡”

በምርመራው ኮሚቴ ውስጥ የተሰየሙት ሰባቱ ዴሞክራቶች፣ ለሰባት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን አመጽ አስመልከቶ፣ ያላቸውን ድርሻ ለማወቅ የቀድሞ የዋይት ሐውስ ረዳቶችን በምርመራዎቻቸው ውስጥ ለማካተት የሚፈልጉ ይመስላል፡፡

በምስክርነት ሂደቱ እየተሰማ ያለው አሳዛኝ ሁኔታ ሊለውጥ የቻለው በኮሚቴው ውስጥ ካሉት ሪፐብሊካኖች መካከል አንዱን ብቻ መሆኑ፣ የዩናትድ ስቴትስን፣ ዝና ለመመለስ ባለው ጥረት ላይ የራሱን ድርሻ እንደሚኖረው ተመልክቷል፡፡

የሪፐብሊካኑ ተወካይ አዳም ኪንዚንገር እንዲህ ይላሉ

“እንደምታውቁት ዴሞክራሲ በመጥፎ ቀኖቻችን የሚተረጎም አይደለም፡፡ ይልቁንም ከእነዚህ መጥፎ ቀናት እንደምን አድርገን እንደምንወጣና ተጠያቂነትን እንዴት አድርገን እንደምንወስድ ይወስነዋል፡፡”

በህዝብ ተወካዮቹ ምክር ቤት የተሰየመው የምርመራ ቡድን እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ምርመራውን እንደሚቀጥል ተመልክቷል፡፡

የምክር ቤቱ የቪኦኤ ዘጋቢ ካትሪ ጊብሰን ከላከችው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG