በሪፐብሊካን ፓርቲ ቁጥጥር ሥር የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት፣ ሲያጨቃጭቅ የሰነበተውን የአገሪቱ በጀት ዛሬ ዐርብ አፅድቋል።
በጀቱ 286 ለ134 በሆነ አብላጫ ድምፅ መጽደቁም ታውቋል። እስከ ቀጣዩ መስከረም ወር ድረስ ለመንግሥት ወጪ የሚውል 1.2 ትሪሊዮን ዶላር ም/ቤቱ ፀድቋል።
በጀቱ በቀጣይ በሕግ አውጪው ም/ቤት ወይም ሴኔት መፅደቅ የሚገባው ሲሆን፣ ሴኔቱ ረቂቁን ተመልክቶ ለማፅደቅ ያለው ጊዜ በሰዓታት የሚቆጠር ነው።
በጀቱ ካልፅደቀ የአሜሪካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ በጀት አይኖራቸውም። በመሆኑም፣ አብዛኞቹ መ/ቤቶች የመዘጋት ዕድል ሊገጥማቸው ይችላል።
በጀቱ መጽደቅ የነበረበት ከስድስት ወራት በፊት ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር። ላለፉት ስድስት ወራት የአሜሪካ ኮንግረስ የተወሰኑ ሳምንታት ወጪዎችን የሚሸፍን የተወሰነ ገንዝብ በመልቀቅ የመንግሥት ሥራ እንዲቀጥል ሲያደርግ ሰንብቷል።
መድረክ / ፎረም