በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህግ አውጭዎች ባይደን የአፍጋኒስታንን ማዕከላዊ ባንክ ገንዘብ እንዲለቁ ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ ፕሬዚዳንት ባይደን
ፎቶ ፋይል፦ ፕሬዚዳንት ባይደን

በርካቶቹ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባል የሆኑ 46 ህግ አውጭ የምክር ቤት አባላት ትናንት ሰኞ ለፕሬዚዳንት ባይደን በጻፉት ደብዳቤ በአፍጋኒስታን እየተባባሰ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ትኩረትና ጊዜ ሰጥተው በአፋጣኝ እልባት እንዲሰጡት አሳሰቡ፡፡

ህግ አውጭዎች ባይደን በአፍጋኒስታን ላይ ተፈጻሚ በመሆን ላይ የሚገኘው ማዕቀብ እንዲላላ፣ ታሊባን አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠረ በኋላ ዋሽንግተን በአፍጋኒስታን ማዕከላዊ ባንክ የውጭ መጠባበቂያ ገንዘብ ላይ የጣለቸውን እገዳ በማንሳት በአስቸኳይ እንድትለቅ በደብዳቤያቸው መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡

ዋይት ሀውስ ትናንት በሰጠው ምላሽ የተያዘውን ገንዘብ አስመልክቶ እጁ የታሰረ መሆኑን ገልጾ በአጋኒስታን የደረሰውን ሰብአዊ ቀውስ ለመርዳት ግን የምታደርገውን ጥረት ትቀጥላለች ብሏል፡፡

የተጣለውን ማዕቀብና በድንገት የተቋረጠው ዓለም አቀፉ ረድኤት ላለፉት 20 ዓመታት በውጭ እርዳታ ጥገኛ ሆኖ የቆየውን የአፍጋኒስታንን ምጣኔ ሀብት በእጅጉ የጎዳው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የአፍጋኒስታን መጣባበቂያ የምንዛሬ ክምችት የሆነውን 9.4 ቢሊዮን ዶላር በመውረስ መያዝዋ ለአፍጋኒስታን ባንኮች ችግር መፍጠሩን፣ በአገሪቱ ላለው የዋጋ ግሽበትም መባባስና የግል ቢዝነሶችንም በመጉዳት ምጣኔ ሀበቱ በከፍተኛ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ማድረጉን የህግ አውጭዎቹ በደብዳቤያቸው አመልክተዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት 40 ሚሊዮን ከሚሆነው የአፍጋኒስታን ህዝብ ግማሽ ያህሉ ለከፍተኛ ረሀብ የተጋለጠ መሆኑን ሲያስታውቅ 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት በከፍተኛ የምግብ እጥረት በሞት አፋፍ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG