በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ዜጎቿ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ በድጋሚ አሳሰበች


አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ ያሉ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች መውጣት አለባቸው ሲሉ በትናንትናው ዕለት በድጋሚ አሳስበዋል።

ስማቸው ያልተገለጸ አንድ የሚኒስቴሩ የቆንስላ ጉዳዮች ቢሮ ተጠሪ በሰጡት ማሳሰቢያ

"ይህን ማሳሰቢያችንን ብዙ ጊዜ ሰምታችሁታል። አሁንም ደግመን እናሳስባችኋለን። በውጭ ሀገር ከሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ደህንነት በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ የለም” ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ቢሮው ባለሥልጣን አክለው ሁሉም ወገኖች ውጊያ አቁመው ድርድር እንዲጀምሩ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ በአካባቢው ካሉ አጋሮቻችን ጋር አብረን በመስራት የተጧጧፈ የዲፕሎማሲ ጥረታችንን እየቀጠልን ሳለንም የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች አሁን የመንገደኛ አውሮፕላን በረራ አማራጩ ባለበት እንዲወጡ የምንወተውተው በዚህ ምክንያት ነው ብለዋል።

ባለፉት በርካታ ቀናት በአዲስ አበባ የጸጥታ ሁኔታ የተለወጠ ነገር እንደሌለ አስተውለናል፤ አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች አሁን ያለውን ሁኔታ በመከታተል ምንም የለም መቆየት እችላለሁ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰው ሊሆን ይችላል ብለን እንሰጋለን። በኛ በኩል ምክረ ሃሳባችን አልተቀየረም፤ አሁኑኑ ውጡ ሲሉ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጦርነቱ እየተካሄደ ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር የአዲስ አበባ የጸጥታ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ሊሄድ ይችላል የሚለውን ሲያጣጥሉ እና ሃገሮች ዜጎቻቸውን እንዲወጡ መወትወታቸውን ሲያወግዙ ቆይተዋል ።

XS
SM
MD
LG