ዋሺንግተን ዲሲ —
ቻይና እኤአ ከ2018 ጀምሮ ካገር እንዳይወጡ አግዳቸው የነበሩ ወንድምና እህት የሆኑ ሁለት አሜሪካውያንን በመልቀቋ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተመልሰዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ በጂንግ አሜሪካውያኑን የለቀቀችው፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በሁዋዌ ሥራ አስፈጻሚ ላይ የመሰረተችውን ክስ ካነሳች በኋላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሲንትያና ቪክተር ሉ የተባሉት አሜሪካውያኑ ምንም የተመሰረተባቸው የወንጀል ክስ ሳይኖር ቻይንና መልቀቅ እንደማይችሉ ተነግሯቸው ላለፉት ሦስት ዓመታት ቻይና ውስጥ ቆይተዋል፡፡
የቀድሞ ባንክ ባለሥልጣልን የነበሩት አባታቸው ሉ ቻንግሚን በቻይና በማጭበርበርወንጀል ተከሰው ይፈለጉ የነበሩ ሰው መሆናቸው ተመልከቷል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታም በካናዳ ታስረው የነበሩት፣ የሁዋዌ ሥራ አስፈጻሚ ሜንግዋንዙ መለቀቃቸውን ተከትሎ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ሁለት የካናዳ ዜጎችም እንዲሁ ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡