በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒዠር ውስጥ ከናይጄሪያ በሚያዋስነው አካባቢ አንድ አሜሪካዊ ግለሰብ መጠለፋቸው ተገለፀ


ኒዠር ውስጥ ከናይጄሪያ ጋር በሚያዋስነው አካባቢ አንድ አሜሪካዊ መጠለፉን የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ፣ ግለሰቡን የጠለፉዋቸው አጋቾች ማስልቀቂያ ገንዘብ መጠየቃቸውም ተገልጿል።

ፊሊፕ ዎልተን የተባሉት አሜሪካዊ ደቡባዊ ኒዠር የገጠር መንደር ከሚገኘው የእርሻ መሬታቸው ላይ ተጠልፈው እንደተወሰዱ የአካባቢው ከተማ ፖሊስ አዛዝ ገልጸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለጉዳዩ የሚያውቅ መሆኑና ለተጠለፉት ሰው ቤተሰቦች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አመልክተዋል። ለጠለፋው ኃላፊ ነኝ ያለ ወገን እስካሁን አልወጣም።

አሜሪካዊው ኒዠር ውስጥ በእስልምና አክራሪ ታጣቂዎች የተጠለፉ ሰባተኛ የውጭ ሃገር ሰው መሆናቸውን ዜናው አክሎ አውስቷል።

XS
SM
MD
LG