በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ እና የቻይና ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣኖች ተነጋገሩ


የአሜሪካ ኤታማዦር ሹም ቻርለስ ብራውን
የአሜሪካ ኤታማዦር ሹም ቻርለስ ብራውን

የአሜሪካ እና የቻይና ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣኖች፣ ከአንድ ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ግዜ ውይይት ማድረጋቸውን እና በርካታ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ የፀጥታ ጉዳይችን በተመለከተ መነጋገራቸውን የአሜሪካ ወታደራዊ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ሁለቱ ወገኖች የግኑኝነታቸውን መሥመር ክፍት አድርገው በሚቀጥሉበት ሁኔታም ላይ ተነጋግረዋል።

በአሜሪካው ኤታማዦር ሹም ቻርለስ ብራውን እና በቻይናው አቻቸው ጄነራል ሊዩ ዜንሊ መካከል በቪዲዮ የተደረገው ውይይት፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ፉክክር ኃላፊነት በሚሰማው መንገድ ስለማድረግና አለመግባባትን በማስወገድ ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

ውይይቱ የመከላከያ ፖሊሲን በተመለከተ እና በኢንዶ ፓሲፊክ ከሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር፣ በባሕር ላይ የሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴን በተመለከተ መወያየት በሚችሉበት መንገድ ላይም አተኩሮ እንደነበር ተመልክቷል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ በቅርቡ በተገናኙበት ወቅት፣ ቻይና ታይዋንን ከግዛቷ ጋር እንደምትቀላቀል ሺ ጂንፒንግ ለባይደን በግልጽ እንደነገሯቸው፣ የኤንቢሲ ቴሌቪዥን የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG