የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የቻይና ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ የቡድን ሰባት ጉባኤን ተከትሎ ወዲያውኑ ሳይሆን በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ እንደሚነጋገሩ ትናንት የብሄራዊ ጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቫን ተናገሩ።
በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በሚቀጥለው ወር ኢንዶኔዥያ ባሊ ውስጥ በሚካሄደው የቡድን ሃያ አባል ሀገሮች ሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ተገናኝተው ለመወያየት ዕቅድ መኖሩን ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች ጠቁመዋል።
የቡድን ሰባት እና የኔቶ አባል ሃገሮች ቻይና ለደቀነቻቸው አደጋዎች ባስቸኩዋይ መፍትሄ መፈለግ እንዳለባቸው የብሄራዊ ጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰሊቫን አሳስበዋል።