በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናና የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ጦርነት


ቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ በሚያካሂዱት መራራ የንግድ ጦርነት ዩናይትድ ስቴትስ ዐይን ያወጣ የኢኮኖሚ አሸባሪነት እየፈፀመች ነው ስትል ቻይና ከሳለች።

የቻይና ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣንግ ሃንሁ ዛሬ ቤዢንግ ላይ ይህን ያሉት ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ በመጪው ሳምንት ሩስያ ላይ ስለሚያካሄዱት ኦፊሴላዊ ጉብኝት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

ቤዢንግና ዋሺንግተን ካለፈው ሀምሌ ወር አንስቶ በኢኮኖሚ ጦርነት ላይ ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በቢልዮኖች ዶላር በሚገመቱ፣ በብዙ መቶዎች በሚቆጠሩ የቻይና ዕቃዎች ላይ ቀረጥ በመጨመራቸው ጥርስን፣ በጥርስ ዓይነት የበቀል ምላሽ አስከትሎ አንዱ በሌላው የንግድ ዕቃ ላይ ቀረጥ ሲጨማመሩ ቆይተዋል።

ቻይና በኢኮኖሚ አሰራርዋ ላይ መዋቅራዊ ለውጥ ለማድረግ የገባችውን ቃል ቀልብሳለች በሚል ትረምፕ በቅርቡ በ200 ቢልዮን ዶላር በሚገመቱ የቻይና ዕቃዎች ላይ ቀረጥ ጨምረዋል።

የቻይናው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ቻይና የንግድ ጦርነት ማካሄድ ባትፈልግም አትፈራውም ብለዋል።

የትረምፕ አስተዳደር ተግባርን “የኢኮኖሚ ማስፈራርያ” ሲሉ ገልፀውታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG