በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና እና የአሜሪካ የንግድ ሥምምነት


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በመጪው ዓመት በሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊሽነፉ ይችላሉ በሚል ተስፋ ቻይና ከአሜሪካ ጋር አዲስ የንግድ ሥምምነት የማድረጉን ጉዳይ እንዳታዘገይ ትረምፕ ዛሬ አስጠንቅቀዋል። ካሸነፉ የሥምምነቱ ደርጃ ከባድ ይሆናል በማለት ዝተዋል።

ከቻይና ጋር “የጥርስን በጥርስ ዓይነት የቀረጥ ጦርነት ላይ ያሉት ትረምፕ ከቤዢንግ ጋር በምናደርገው ድርድር “ዩናይትድ ስቴትስ በጥሩ ይዘት ላይ ትገኛለች” ብለዋል።

እነሱ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በሚያደርጉት የንግድ መትረፍረፍ በመቶዎች ቢልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከአሜሪካ በመዝረፍ ተግባራቸው ለመቀጠል ሲሉ ከአዲስ አስተዳደር ጋር መስራቱን ይመርጣሉ። ነገር ግን በመጪው ዓመት በአዲስ ፕሬዚዳንት እስከሚተኩበት ጊዜ ድረስ የሥራ ዕድሎችንና ኩባንያዎችን ማድማቱ ረዥም ጊዜ ይሆናል ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG