ዋሺንግተን ዲሲ —
የመንግሥት ይዞታ የሆነው ሽንዋ የዜና አገልግሎት በገለፀው መሰረት ምክትል የገንዘብ ሚኒስትር ሊዮ ሚነ ነገ ዋሽንግተን ይገባሉ። ዋሽንግተን ለሚካሂደው የከፍተኛ ደረጃ ድርድር ለማመቻቸት ሲሉ ከትራምፕ አስተዳደር አቻዎቻቸው ጋር ይነጋገራሉ።
ሁለቱ ሀገሮች በያዝነው ወር ቀደም ሲል አዲስ የንግግር ዙር ለማካሄድ የወሰኑት የቻይና ዋና ተዳራዳሪ የሆኑት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሉ ሂና የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ተወካይ ሮበርት ላይትዘር እና የገንዘብ ሚኒስትር ስቲቭን ምኑቺን በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ ነው።
ሁለቱም ሀገሮች ባለፈው ሃምሌ ወር አብይ ንግግር ያካሄዱ ቢሆንም በሁለቱ የኢኮኖሚ ቁንጮዎች መካከል ያለውን የንግድ ጠብ ለማርገብ አልቻሉም።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ