በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ሽቀጥ ላይ ቀረጥ ጨመረች


ፎቶ ፋይል፡-የአሳማ ሥጋ
ፎቶ ፋይል፡-የአሳማ ሥጋ

ዩናይትድ ስቴትስ በ200 ቢልዮን ዶላር በሚገመት የቻይና ሸቀጥ ላይ ከ 10 እስከ 25 ከመቶ ቀረጥ ጨምራለች። ቻይና ግን የቀረጥ መጠኑን ከፍ ብታደርግም “የጥርስን በጥርስ” ዓይነት የ”በቀል” ምላሽ ውስጥ አልገባችም። ቻይና በሌላ መንገድ ጉልበትዋን እያሳየች መሆንዋ ተገልጿል።

ቻይና ባልተጠበቀ መልኩ ከአሜሪካ የምታስገባውን የአሳማ ሥጋን በ6.5 ቢልዮን ዶላር ቀንሳለች። ቻይና የአሜሪካን የአሳማ ሥጋን በብዛት በማስገባት በኩል ሁለትኛዋ ሀገር ስለነበረች የዩናይትድ ስቴትስ የአሳማ ሥጋ አምራች ገበሬዎችን ክፉኛ ጎድቷል።

የቻይና የአሳማ ዕርብታ በአፍሪካ የአሳማ ትኩሳት በሽታ በተጎዳበት በአሁኑ ወቅት ቻይና እንዲህ ዓይነት ዕርምጃ ትወስድለች የሚል ግምት አልነበረም ተብሏል።

ተንታኞች እንደሚሉት ቻይናን ከአሜሪካ የሚለየው አንድ ነገር ህዝቧ የመንግሥቱን ፍላጎት የሚያከብር መሆኑ ነው። ሀገሪቱ ከፍተኛ ቀረጥ የተጣለባቸውን ከአሜሪካ የሚገቡ ዕቃዎችን መግዛቱን ብትቀንስም እንኳን ህዝቡ መቀበሉ አይቀሬ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG