በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካና የቻይና የንግድ ንግግር በውጥረት ቀጥሏል


ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና እያካሄዱ ካሏቸው ውዝግብና ውጥረት የበዛባቸው የንግድ ድርድሮች ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰጠው ብዙ እንደሌለና ከቤጂንግ ግን የበዛ እንደሚጠበቅ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ።

ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና እያካሄዱ ካሏቸው ውዝግብና ውጥረት የበዛባቸው የንግድ ድርድሮች ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰጠው ብዙ እንደሌለና ከቤጂንግ ግን የበዛ እንደሚጠበቅ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ ለዚህ ሃሣባቸው መሠረት ያደረጉት እጅግ ለበርካታ ዓመታት ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ ተጠቃሚ ሆና መቆየቷን እንደሆነ ተናግረዋል።

ዚቲኢ የሚባለው ግዙፉ የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያ ዋሺንግተን በኢራንና በሰሜን ኮሪያ ላይ ጥላቸው የነበሩ እገዳዎችን ጥሶ ሲናገድ ተይዟል በሚል ከአሜሪካ የንግድ ተቋማት ላይ ግብአቶችን እንዳይገዛ በዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ሚኒስቴር የሰባት ዓመት ክልከላ ደንግጎበት የነበረ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ ያንን ክልከላ ያነሱበትን ምክንያት ዛሬ በትዊተር ባሠራጩት መልዕክት ተከላክለዋል።

እነዚያን በአሜሪካ ኩባንያዎች የሚመረቱ ዕቃዎችን ማግኘት ባለመቻሉ ከእንቅስቃሴው የበዛውን ለማቆም ተገድዶ እንደነበር ዚቲኢ አስታውቋል።

“ዚቲኢ የዋናው የንግድ ድርድር አካል ከመሆኑ በስተቀር የደረሰበት ምንም የለም” ብለዋል ፕሬዚዳንት ትረምፕ።

በዓለም እጅግ ግዙፎቹ ምጣኔ ኃብቶች የሆኑት ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና ሰሞኑን ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ተቀምጠው በከበዱ የንግድ ንግግሮች ተጠምደዋል።

በቻይና ወጭ ንግድ ላይ የ150 ቢሊየን ተመን ያለው ታሪፍ እንደሚጥሉ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ከዛቱ በኋላ ቻይና አፀፋውን በዓይነት እንደምትመልስና በአሜሪካ ምርቶች ላይ ከዚያ የበዙ ታሪፎችን እንደምትደነግግ በመግለፅ አስጠንቅቃ ነበር።

ቀደም ሲል ቤጂንግ ላይ የተካሄዱ ንግግሮች ያለፍሬ ተፈፅመዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG