በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለታይዋን ሚሳዬል ለመሸጥ ማቀዷን ቻይና ተቃወመች


ፎቶ ፋይል፦ ኤፍ 16 ተዋጊ ጀት
ፎቶ ፋይል፦ ኤፍ 16 ተዋጊ ጀት

የባይደን አስተዳደር ለታይዋን በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤፍ 16 ተዋጊ ጀቶችና ሚሳዬሎችን ጨምሮ የ651 ሚሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ለማጽደቅ መወሰኑን ቻይና አውግዛለች።

ሩሲያ የዩክሬኑን ጦርነቷን እንድታሸነፍ ቻይና የጦር መሳሪያ ድጋፍ ልታደርግላት ትችላለች ብለው ምዕራባውያን በሰጉበት በዚህ ወቅት፣ በዋሽግንተን እና በቤጂንግ መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ መድረሱም ተነግሯል።

በዚህ ሳምንት በባይደን አስተዳደር ለምክር ቤቱ በቀረበው የ619 ሚሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነት መሰረት ታይዋን የኤፍ 16 ተዋጊ ጀቶችን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳዬሎችና ተያያዥ መሳሪያዎችን ታገኛለች ተብሏል።

እርምጃው የታይዋንን ሉአላዊነትና የሚጥስ ነው ሲሉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ሚንግ ተናግረዋል።

በቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና በሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን መካከል ስብሰባ ለማድረግ መታቀዱም ታውቋል።

XS
SM
MD
LG