በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የንግድ ንግግር ማድረግ አይቻልም አለች


ፎቶ ፋይል

አዲሱ ዙር የቀረጥ ሕግ ተግባር ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የንግድ ንግግር ማድረግ አይቻልም ስትል ቻይና አስታውቃለች።

አዲሱ ዙር የቀረጥ ሕግ ተግባር ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የንግድ ንግግር ማድረግ አይቻልም ስትል ቻይና አስታውቃለች።

ዩናይትድ ስቴትስ $200 ቢሊዮን በሚያወጣ የቻይና የንግድ ቁሳቁስ ላይ ቀረጥ የጣለች ሲሆን፣ ቻይናም ከዛሬ ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውል $60 ቢሊዮን በሚጠጋ የዩናይትድ ስቴትስ ሸቀጦች ላይ የአፀፋ ዕርምጃ ወስዳለች።

የቻይናው ምክትል የንግድ ሚኒስትር ዛሬ ቤይጂንግ ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፣ “የትራምፕ አስተዳደር ይህን የመሰለ ግዙፍ ቀረጥ በጣለበት ሁኔታ ምን ዓይነት የንግድ ንግግር ማድረግ ይቻላል” ሲሉ ጠይቀዋል። ሁኔታውንም “በአንድ ሰው ጉሮሮ ላይ ጩቤ ደግኖ እንደማስገደድ” ዓይነት ነው ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ምርቶች ላይ አዲስ የጣለቸው ቀረጥ የኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች፣ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችን ያካትታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG