በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ቀረጥ የመጣል ዕቅድ ተግባራዊ ካደረገች ቻይና አፀፋ እንዳላት ተናገረች


ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ ቀረጥ ልትጥልብን ያላትን ዕቅድ ተግባራዊ ካደረገች ተገቢውን አፀፋ እመልሳለሁ ስትል ቻይና ተናገረች።

ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ ቀረጥ ልትጥልብን ያላትን ዕቅድ ተግባራዊ ካደረገች ተገቢውን አፀፋ እመልሳለሁ ስትል ቻይና ተናገረች።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የመንግሥታቸው የንግድ ተወካይ ቻይና በምትልከው የሁለት ቢሊዮን ዶላር ሸቀጥ የአሥር ከመቶ ቀረጥ ሊጣልበት የሚገባቸውን ምርቶች ዝርዝር እንዲያወጣ መጠየቃቸውን ትናንት አስታውቀዋል።

ይህን ያደረጉት ቤጂንግ ለመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ የቀረጥ ጭማሪ አፀፋ ለመመለስ ዩናይትድ ስቴትስ በምትልከው የሃምሳ ቢሊዮን ዶላር ሸቀጥ ላይ ቀረጥ ለመጣል ያደረገችውን ውስኔ ለመበቀል መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

የቻይና የንግድ ሚስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የኋለኛው የሚስተር ትረምፕ ዕርምጃ በተላያዩ ጊዜያት ባደረግናቸው ውይይቶች ከደረስንባቸው ሥምምነቶች የወጣ የየዕለት ጫና የማሳደርና የማስፈራራት ተግባር ነው ብሎታል።

በሁለቱ ሀገሮች መካከል በተያዘው ቁርቁዋሶ ምክንያት የእስያ የአክስዮን ዋጋ ዛሬ አአሽቆልቁሎ ውሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG