ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ባለፈው ኅዳር ወር፣ ካሊፎርኒያ ሳን ፍራንሲስኮ ከተማ ላይ ከተካሔደው የእስያ ፓሲፊክ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር የመሪዎች ጉባኤ ጎን ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ወቅት፣ ፕሬዚዳንት ሺ፣ በሀገራቱ ግንኙነት አስቸጋሪ የኾነው የታይዋን ጉዳይ እንደኾነ፣ ለፕሬዚዳንት ባይደን ነግረዋቸዋል።
የቪኦኤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ዋና ዘጋቢ ናይኪ ቺንግ፣ ደሴቲቱ በሁለቱ ልዕለ ኀያላን ግንኙነት ያላትን ስፍራ የሚያስቃኝ ዘገባ አጠናቅራለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም