በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና የቀይ ባሕር መርከቦችን በመጠበቁ ለምን አትሳተፍም?


ቻይና የቀይ ባሕር መርከቦችን በመጠበቁ ለምን አትሳተፍም?
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:04 0:00

ቻይና የቀይ ባሕር መርከቦችን በመጠበቁ ለምን አትሳተፍም?

በቀይ ባሕር ዔደን ባሕረ ሰላጤ፣ ሰኞ ከሁቲ ዓማፅያን በተተኮሰ ሚሳየል የተመታ መርከብ ጉዳት ደርሶበታል።

በኢራን የሚደገፉት የየመን የሁቲ ዓማፅያን፣ በዔደን ባሕረ ሰላጤ እና በቀይ ባሕር በሚጓዙ ዓለም አቀፍ የመርከብ መሥመሮች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ቀጥለውበት ይገኛሉ። በአንጻሩ፣ ዩናይትድ ስቴትስንና እንግሊዝን ጨምሮ የ24 ሀገራት ጥምረት፣ የውኃ አካሉን ደኅንነት ለመጠበቅ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በአውሮፓ እና በእስያ መካከል፣ 40 ከመቶ የሚደርሰው የንግድ ልውውጥ በአካባቢው የሚተላለፍ ቢኾንም፣ ቻይና በጥምረቱ ውስጥ እንደማትሳተፍ ይታወቃል።

ቻይና የቀይ ባሕር መርከቦችን በመጠበቁ ለምን አትሳተፍም? የሚል ጥያቄን ያነሣችው የቪኦኤ ዘጋቢዋ ካርላ ባብ ከፔንታገን፣ ተጨማሪ ዘገባ አድርሳናለች፤ ደረጀ ደስታ ያቀርበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG