በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካና ቻይና ስለኑክሌር ሊነጋገሩ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የቻይናን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን
ፎቶ ፋይል፦ የቻይናን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን

ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና ስለ መሣሪያ ቁጥጥርና እሽቅድምድም ጉዳይ በሚቀጥለው ሣምንት ውስጥ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ እንደሚመክሩ የቻይናን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢንን ጠቅሶ ሮይተርስ ዛሬ ዘገበ።

ቻይና ማንነታቸውን ባታሳውቅም ለምክክሩ የመሣሪያ ቁጥጥር መሥሪያ ቤቷን ‘ዋና’ የተባሉ ባለሥልጣን እንደምትልክ ይፋ አድርጋለች።

የባለሥልጣናቱ ውይይት ዓለምአቀፍ የመሣሪያ ቁጥጥር ስምምነቶችን ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም እንደሚያተኩር ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ሰሞኑን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ተገኝተው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን ጨምሮ ከከፍተኛ ባለሥልጣናቱ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን ሁኔታውን ሁሉም ወገኖች እጅግ የበረቱ የፖሊሲ ልዩነቶች ባሏቸው በሁለቱ ጂዖፖለቲካዊ ኃያላን ተቀናቃኞች መካከል “የግንኙነቱን መሥመር ጠብቆ ለማቆየት መልካም ዕድል እንደፈጠረ” አጋጣሚ እንደተመለከቱት ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG