በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት የዓለምን ሰላም አደጋ ላይ እንደሚጥል አሜሪካ አስጠነቀቀች


 ፎቶ ፋይል፦ የቤጂንግ ማዕከላዊ ቢዝነስ ዲስትሪክት እአአ ሚያዝያ 30/2023
ፎቶ ፋይል፦ የቤጂንግ ማዕከላዊ ቢዝነስ ዲስትሪክት እአአ ሚያዝያ 30/2023

ቻይና፣ በመላው ዓለም ሐሰተኛ መረጃ እያሠራጨች እንደኾነች የከሰሰው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ሉላዊውን ሰላም እና መረጋጋት አደጋ ላይ እንደሚጥል አስጠነቀቀ፡፡

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በጉዳዩ ላይ ባወጣው ሪፖርት፣ በመላው ዓለም ቻይናን አስመልክቶ ያለውን ትርክት ለመቀየር፣ ቤጂንግ የምታደርገውን ጥረት አትቷል። ያንንም ለመፈጸም በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ በማፍሰስ ላይ እንደኾነች አስታውቋል፡፡

የብዙኀን መገናኛ ውጤቶችን መሸመት፣ ሐሳዊ ማንነትን በመፈብረክ የቤጂንግን መልዕክት በሰፊው ማሰራጨት፣ ቤጂንግን የሚያሳጡ አካውንቶችን ማዘጋት፣ የሐሰተኛ መረጃ ዘመቻው አካል እንደኾነ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ሪፖርት ዘርዝሯል።

የቤጂንግ ዓለም አቀፍ የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት፣ በመላው ዓለም በሚሰጡ ውሳኔዎች እና በአሜሪካ ጥቅም ላይ ተጽእኖ የማስከተል ዐቅም ሊኖረው እንደሚችል፣ መ/ቤቱ አስጠንቅቋል።

ሪፖርቱን ያወገዘችው ቤጂንግ፣ ሪፖርቱ በራሱ “ሐሰተኛ መረጃ ነው” ስትል አጣጥላዋለች፡፡

“እንደተለመደው፣ ቻይናን የማሳነስና የአሜሪካን የበላይነት የማጉላት ዓላማ ያለው ነው፤” ሲል፣ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ምላሽ ሰጥቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG